አላህ በባሪያው ላይ ከዋለው ችሮታዎች መካከል አንዱ ማንኛውም የአላህ ባሪያ እጅግ የላቀ ምንዳን ይቀዳጅ፣ ይጠበቅ፣ ይከላከል፣ የነቢዩን (የአላህ ሰላምና እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁን) አርአት ተከታይ ይሆን ዘንድ ከጠዋት አንስቶ ማታ ወደመኝታው እስኪያመራ ድረስ ዚክሮችን ከእሱ ጋር እንዲቆራኙ ማድረጉ ነው፡፡
ማመልከትአንድ የአላህ ባሪያ ቀኑን የልእልና ባለቤት የሆነውን አላህን በማስታወስ እንዲያካብብ፣ አላህን በማውሳትም ከሰይጣኖች ጉትጎታ እንዲጠበቅ እንዲሁም ‹‹ ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው፡፡›› (ቃፍ ፡ 39) ለሚለው የአላህ ቃል ምላሽ በመስጠት የነቢዩን (የአላህ ሰላምና እዝነት በእሳቸው ላይ ይሁን) ፈለጎች ተምሳሌት አድርጎ እንዲከተል አላህ (ሱ.ወ) ባሪያዎቹ የጠዋት እና የምሽት አዝካሮችን እንዲሉ አነሳስቷል፡፡
ማመልከትትክክለኛው ጎህ ሲቀድ አንድ ሙስሊም የዚክርና የመጠበቂያ ልብሶችን ልእልና የተገባው አላህ፤ ‹‹ ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው፡፡›› በማለት የተናገረውን ለመተግባር፣ የቀን ተግባራቱ ጅማሮ እንዲሆንና በትእዛዝ ላይ የታነጸ ይሆን ዘንድ ይለብሳል፡፡
ማመልከትአጫጭር የሆኑ የቁርአን ምዕራፎችንና ትክክለኛ የሆኑ አዝካሮችን ምንም ችግር በሌለበት ዘዴ እንዲያነቡ የሚያስችልዎትን የምናቀርብልዎ አገልግሎት ነው፡፡
. በተደጋጋሚ በደንብ ማጥናትንና በትክክል ቃሉን ማንበብ ለማረጋገጥ ማስቻል
. የድምጽ ፋይሎችን እጅግ ውብ የሆኑ ድምጽ ባለቸው አንባቢዎች እናቀርብልዎታለን
መማርዎትን ይጀምሩ