languageIcon
search
search
brightness_1 মাগরিবের প্রথম ওয়াক্তের সঙ্গে সঙ্গে বাচ্চাদের ঘরের ভেতরে রাখা সুন্নাত।

এই দু’টি সুন্নাত মানুষকে জ্বিন ও শয়তান থেকে সুরক্ষার নিশ্চয়তা দেয়। সন্ধ্যার সময় শয়তান চারদিকে ছড়িয়ে পড়ে। সুতরাং সেই সময়টাতে বাচ্চাদের ঘরের ভেতরে রাখা ও আল্লাহর নাম নিয়ে ঘরের দরজা বন্ধ করা সকলের সুরক্ষা নিশ্চিত করে। বাস্তব অভিজ্ঞতায় দেখা গেছে, অসংখ্য বাচ্চা ও ঘরবাড়ির ওপর এই সময় জিন-ভূত আছর করে থাকে। আর এভাবেই বোঝায় যায়, আমাদের ছেলে-সন্তান ও ঘর-বাড়ির সুরক্ষার প্রতি ইসলাম কতটা যত্নবান।

এর দলীল হচ্ছে:

জাবের বিন আব্দুল্লাহ রা. এর হাদীস। তিনি বলেন, রাসূলে কারীম (সাল্লাল্লাহু আলাইহি ওয়া সাল্লাম) বলেছেন, ‘যখন রাত অন্ধকার হয়ে আসে-অথবা যখন সন্ধ্যা হয়- তোমরা তোমাদের সন্তানদের নিজেদের কাছে রাখো। কারণ সে সময় শয়তান চারদিকে ছড়িয়ে পড়ে। এরপর যখন রাতের এক প্রহর চলে যায়, তখন তাদেরকে ছেড়ে দাও, ঘরের দরজা বন্ধ করো এবং আল্লাহর নামের যিকির করো। কেননা শয়তান কোনো বন্ধ দরজা খুলতে পারে না’। (বুখারী ৩৩০৪, মুসলিম ২০১২)

উল্লেখ্য, মাগরিবের সময়টাতে  বাচ্চাদের নিজেদের কাছে রাখা, দরজা বন্ধ করা ইত্যাদি ফরজ বা ওয়াজিব নয়; মুস্তাহাব আমল। দেখুন- ফাতওয়ায়ে লাজনা দায়েমা ২৬/৩১৭)

brightness_1 በመግሪብ የመጀመሪያው ወቅት ላይ በሮችን መዝጋትና -በእጅጉ የላቀውን- አላህን ማውሳት፡፡

እነዚህ ሁለት ተግባራት መፈጸም ከሸይጣኖችንና ከአጋንንት መጠበቂያ ነው፡፡ በመግሪብ የመጀመሪያው ወቅት ሕጻናትን መሰብሰብ በዚያ ወቅት ከሚሰራጩ ሸይጣኖች ሕጻናቱን መጠበቂያ ነው፡፡ በዚሁ ወቅት ላይ  በሮችን መዝጋትን -እጅግ የላቀውን- አላህን ማውሳት እንዲሁ መጠበቂያ ነው፡፡ ስንት ሕጻናት ናቸው በዚህ ወቅት ሳይከለከሉ በሸይጣኖች የተለከፉት፡፡ ይህ ዓይነቱ ኢስላም ለሕጻናቱና ለቤታችን ያደረገው ትልቅ እንከብካቤና ጥበቃ እንዴት አያስደስትና አያስገርም!

ለዚህ ማስረጃው፡-

ጀቢር ኢብን ዐብዲላህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “የምሸቱ ክፍል ሲሆን -ስታመሹ- ሕጻናቶቻችሁን ሰብስቡ፡፡ በርግጥ ሸይጣኖች በዚህ ጊዜ ይሰራጫሉ፡፡ ከምሽቱ የተወሰነ ጊዜ ሲያልፍ ተዉዋቸው፡፡ በሮችን ዝጉ፡፡ አላህንም አውሱ፡፡ በርግጥ ሸይጣን የተዘጋን ቤት    አይከፍትም፡፡” ብለዋል፡፡ ቡኻሪ ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (3304)፣ ሙስሊም ደግሞ በቁጥር (2012) ላይ ዘግበውታል፡፡

ሕጻናትን መሰብሰብና በሮችን መዝጋት የሚወደድ ተግባር ከመሆኑ አንጻር ነው ተግባራዊ የሚሆነው፡፡ ፈታዋ ለጅነቱ አድ-ዳኢመህ ቅጽ ፡ 26 ገጽ ፡ 317፡፡

brightness_1 ከመግሪብ ሰላት በፊት ሁለት ረከዐዎችን መስገድ

ዐብዱላህ ኢብን መገፍፈል -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ከመግሪብ በፊት ስገዱ” አሉና ሰዎች ነቢያዊ ፈለግ አድርገው እንዳይዙት ጠልተው በሶስተኛው ላይ፣ “ለፈለገ ሰው፡፡” አሉ፡፡›› ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲ ዘገባ ቁር (1183) ላይ ዘግበውታል፡፡

- እንዲሁ በእያንዳንዱ አዛንና ኢቃመህ መካከል ሁለት ረከዐዎችን መስገድ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡

እነዚህ ሁለት ረከዐዎች እንደፈጅር፣ ዙህር ዓይነት ከሆኑ ብርቱ የሆኑ የሱንና ሰላቶችን መስገድ እነዚህን ሰላቶች ያብቃቃል፡፡ ወይም ሰውዬም መስጂድ ተቀምጦ ከሆነና ሙአዚኑ ለዐስር ወይም ለዒሻእ ሰላት አዛን ያደረገ እንደሆነ ተነስቶ ሁለት ረከዐዎችን መስገዱ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡

ለዚህ ማስረጃው፡-

ዐብዱላህ ኢብን አል-መገፍፈል አል-ሙዘኒይ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-ሶስት ጊዜ፣ “በእያንዳንዱ ሁለት አዛኖች መካከል ሰላት አለ፡፡” አሉና በሶስተኛው ላይ፣ “ለፈለገ ሰው” አሉ፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (624)፣ ሙስሊም ደግሞ በቁጥር (838) ላይ ዘግበውታል፡፡

ከመግሪብ  በፊትና በእያንዳንዱ ሁለት አዛኖች መካከል የሚሰገዱት ሁለት ረከዐዎች ብር እንደሆኑት የሱንና ሰላቶች አይደሉም፡፡ ምናልባትም አንዳንድ ጊዜ ሊተዉ ይችላሉ፡፡ ለዚህም ነው ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- በሐዲሣቸው ላይ ሰዎች ነቢያዊ ፈለግ አድርገው እንዳይዙት በመጥላት “ለፈለገ ሰው”  ያሉት፡፡