languageIcon
search
search
brightness_1 በጣም ሞቃትማ በሚሆንበት ጊዜ ሙቀቱ ጋብ እስከሚል ድረስ ማዘግየት ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡

ለዚህ ማስረጃው፡-

አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝንትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ሙቀቱ ከበረታ ሰላትን አቀዝቅዙ፡፡ የሙቀት በርቱነት ከጀሃነም እስትንፋስ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (533፣534)፣ ሙሰሊም ደግሞ በቁጥር (615) ላይ ዘግበውታል፡፡

ሸይኽ ኢብን ዑሠይሚን -አላህ ይዘንላቸው-፣ ‹‹ጸሐይ በበጋ ወቅት ስድሰት ሰአት ላይ ከአናት ታዘንፋለች፣ የዐሰር ወቅት በግምት አስር ሰአት ተኩል ላይ ነው ብለን ብንገምት፣ የማቀዝቀዣው ሰአት ወደአስር ሰአት ገደማ ነው ማለት ነው፡፡›› አል-ሙምቲዕ  ቅጽ ፡ 2 ገጽ ፡ 104፡፡

ማቀዝቀዙ በሕብረት ለሚስግዱም ሆነ ለብቻው ለሚሰግድ ሰው አጠቃላይ ነው፡፡ ሸይኻችን ኢብን ዑሠይሚን -አላህ ይዘንላቸው- ይህን መርጠዋል፡፡ በዚህ ሥር ሴቶችም ይጠቃለላሉ፡፡ ሴቶችም ሙቀቱ ብርቱ በሚሆንበት ወቅት ማቀዝቃዝ ነቢያዊ ፈለግ መከተል ተደርጎ ይቆጠርላቸዋል፡፡ ይህም አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ያስተላለፉት ሐዲሥ ሁሉንም የሚያጠቃልል ስለሆነ ነው፡፡