languageIcon
search
search
brightness_1 በተክቢረተ-ል-ኢሕራም ላይ እጆችን ከፍ ማድረግ

ኢብን ዑመር -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት፣ ‹‹የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ሰላታቸውን ሲጀምሩ፣ ሩኩዕ ለማድረግ አላሁ አክበር ሲሉ እንዲሁም ከሩኩዕ ሲነሱ እጆቻቸውን እስከትከሻቸው ድረስ ከፍ ያደርጉ ነበር፡፡ ከሩኩዕ ሲነሱ፣ “ሰሚዐ-ልላሁ ሊመን ሐሚደህ ረብበና ወለከልሐምድ /አላህ የአመስጋኙን ምስጋና አዳመጠ፣ ጌታችን ሆይ! ምስጋናም ላንተ ነው፡፡/” ይሉ ነበር፡፡ ይህን ሱጁድ ላይ አይተገብሩም ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ ቡኻሪ ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (735)፣ ሙስሊም ደግሞ በቁጥር (390) ላይ ዘግበውታል፡፡  

ኢብን ሁበይራህ -አላህ ይዘንላቸው- እንዲህ ብለዋል፣ ‹‹በተክቢረቱ-ል-ኢሕራም ወቅት እጆችን ማንሳት ነቢያዊ ፈለግ በመሆኑ ላይና ግዴታ ባለመሆኑ ላይ ዑለሞች ሀሃሳባቸውን አንድ አድርገዋል፡፡›› አል-አፍሳሕ ቅጽ ፡ 1 ገጽ፡ 123፡፡ 

ይህ በተክቢረቱ-ል-ኢሕራም ወቅት እጆች የሚነሱበት ሥፍራ ዑለሞች የተስማሙበት ሥፍራ ነው፡፡ በሌሎች ሥፍራዎች ላይ እጆችን ማንሳት በተመለከተ በዑለሞች -አላህ ይዘንላቸው- ዘንድ የሃሳብ ልዩነት አለ፡፡

በሐዲሥ የተዘገቡት እጆች የሚነሱባቸው የሰላት ቦታዎች አራት ናቸው

የመክፈቻው ተክቢራህ ላይ

ረኩዕ ላይ

ከረኩዑ በመነሳት  ላይ

እነዚህ ሶስቱ ከኢብን ዑመር -አላህ መልካምሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ከዚህ በፊት እንደተመለከተው በሁለቱ የሐዲሥ ዘገባዎች የተረጋገጡ ናቸው፡፡ አራተኛው ርዕስ፡-

ከመጀመሪያው ተሸሁድ (አት-ተሒያቱ) በሚነሱ ጊዜ

ይህ ከኢብን ዑመር -አላህ መልካምሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዲሁ የተረጋገጠ በሆነው  በሰሒሑ-ልቡኻሪ ዘገባ ውስጥ ሰፍሮ የሚገኝ ነው፡፡

 

brightness_1 በቀኝ እጁ የግራ እጁን አጥብቆ መያዝ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡

የመጀመሪያው ሁኔታ፡- ቀኝ እጁን በግራ እጁ ላይ ያስቀመጣል፡፡ ዋኢል ኢብን ሐጀር -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ሰላት ላይ ሲቆሙ በቀኝ እጃቸው የግራ እጃቸውን ሲይዙ ተመልክቻለሁ፡፡›› ብለዋል፡፡ አቡ ዳዉድ ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (755) እንዲሁም አን-ነሳኢይ በቁጥር (888) የዘገቡት ሲሆን አል-አልባኒይም ትክክለኛቱን አረጋግጠዋል፡፡ 

ሁለተኛው ሁኔታ፡- የቀኝ እጁን በግራ ክንዱ ላይ  ያስቀምጣል፡፡  ሰህል ኢብን ሰዕድ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸው- እንዲህ ብለዋል፣ ‹‹ሰዎች አንድ ሰው ሰላት ውስጥ ቀኝ  እጁን በግራ ክንዱ ላይ እንዲያደርግ ይታዘዙ ነበር፡፡›› ቡኻሪ ሐዲሡን ነሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (740) ላይ ዘገበውታል፡፡

በዚህ መሰረት የሚሰግደው ሰው ነቢያዊ ፈለጉን ለመከተል አንዳንድ  ጊዜ ቀኝ እጁን በግራ እጁ ላይ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በግራ ክንዱ ላይ በማስቀመጥ እያቀያየረ መፈጸም ይችላል፡፡ 

brightness_1 የሰላት መክፈቻ ዱዓእ ማድረግ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡

የሰላት መክፈቻ ዱዓእ አገላለጽ የተለያየ ነው፡፡ ይህን ዱዓእ በተለያየ ሁኔታ ማለት የተወደደ ነው፡፡ በሐዲሥ ላይ ከተዘገቡ የሰላት መክፈቻ ዱዓእ መካከል፡-

ሀ. ‹‹ሱብሓነከ-ልላለሁምመ ወቢሐምዲከ፣ ወተባረከ-ስሙከ፣ ወተዓላ ጀድዱከ ወላ ኢላሀ ገይሩከ፡፡/ጠራት የተገባህ አላህ ሆይ! ምስጋናም ላንተ ነው፡፡ ስምህም የተባረከ ነው፡፡ ክብርህም የላቀ ነው፡፡ በእርግጥ ካንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡/›› አህመድ ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (11473)፣ አቡ ዳዉድ በቁትር (776)፣ አት-ቲርሚዚይ በቁጥር (243) እንዲሁም አን-ነሳኢይ በቁጥር (900) ዘግበውታል፡፡ ሐዲሡ የሚጠናከርበት የተለያዩ መንገድች ያሉ ሲሆን ኢብን ሐጀር የሐዲሡን በጥሩ ደረጃ መገኘት አረጋግጠዋል፡፡ (አል-አፍካር ቅጽ ፡ 1 ገጽ ፡ 412)፡፡

ለ. ‹‹አል-ሐምዱ-ሊልላሂ ሐምደን ከሢይረን ጠይዪበን ሙባረከን ፊይሂ /በርካታ፣ ያማረና በርከት ያለበት ምስጋና ለአላህ ነው፡፡/›› የዚህ ምስጋና ትሩፋት አስመልከተው የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- እንዲህ ብለዋል፣ “ማናቸው ያነሷት ዘንድ አስራ ሁለት መላእክቶች ሲሽቀዳደሙባት በርግጥ ተመልክቻለሁ” ሐዲሡን ሙሰሊም ከአንስ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (600) ዘግበውታል፡፡

ሐ. “አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጣያየ ከማ በዐድተ በይነ-ል-መሽሪቂ ወል-መግሪብ፡፡ አልላሁምመ ነቅቂኒ ሚን ኸጣያየ ከማ ዩነቀ አሥ-ሠውቡ-ል-አብየዱ ሚነ-ድደነስ፡፡ አልላሁምመ ኢግሲልኒ ሚን ኸጣያየ ቢሥሠልጂ ወል-ማኢል ወል-በረዲ፡፡/አላህ ሆይ! በምስራቅና በምዕራብ እንዳራራቅከው በእኔና በሐጢአቶቼ መካከል አራርቅ፡፡ አላህ ሆይ! ነጭ ልብስ ከእድፍ እንደሚነጻ ሁሉ ከሐጢአቶቼ አንጻኝ፡፡ አላህ ሆይ! በበረዶ፣በውሃና በበቀቅ ከሐጢአቶቼ እጠበኝ፡፡/” ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (744)፣ ሙስሊም ደግሞ በቁጥር (598) ከአቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ዘግበውታል፡፡  

መ. “አለሁ አክበር ከቢራ፣ ወልሐምዱ ሊልላሂ ከሲይራ፣ ወሱበሓነ-ልላሂ ቡክረተን ወአሲይላ፡፡/አላህ በእጅጉ መተለቅን ታላቅ ነው፡፡ በርካታ ምስጋና ለአላህ ይገባው፡፡ አላህ ዛሬም ምንጊዜም ከሚባለው ውድቅና የማይረባ ንግግር የጠራ ነው፡፡” የዚህን ዱዓእ ትሩፋት አስመልክተው የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “በጣም ተደነቄላታለሁ፡፡ የሰማያት በሮች ተከፈቱላት፡፡” ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (601) ከዚህ በላይ ባሳለፍነው የኢብን ዑመር -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ዘግበውታል፡፡

brightness_1 በአላህ ሥም መጀመር፡፡

ከሸይጣን በአላህ ከተጠበቁ በኋላ አንድ ሰው በአላህ ሥም የቁርኣን ንባቡን መጀመሩ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡ እንዲህም ይላል፣ ‹‹ቢስሚ-ልላሂ-ርረሕማኒ-ርረሒይም፡፡ /በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡/››፡፡ ይህ ከነዒም አል-ሙጀመር -አላህ መልካም ሥራዎቸውን ይውደድላቸው- ከተወራ ሐዲሥ የተወሰደ ነው፡፡ በዚህ ሐዲሥ ላይ ነዒም እንዲህ ብለዋል፣ ‹‹ከአቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ኋላ ሰገድኩኝ፡፡ “ቢስሚ-ልላሂ-ርረሕማኒ-ርረሒይም፡፡”ን አነበቡ፡፡ ከዚያ የአል-ፋቲሐን ምዕራፍ አነበቡ፡፡›› በዚሁ ሐዲሥ ላይም፣ ‹‹ነፍሴ በእጁ በሆነችው አላህ እምላለሁ! የአላህ መልእክተኛን -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ሰላት አስመስልላችኋላሁ፡፡›› ብለዋል፡፡ አን-ነሳኢይ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (906) እንዲሁም ኢብን ኹዘይመህ የዘገቡት ሲሆን ትክክለኛነቱንም አረጋግጠዋል (ቅጽ ፡ 1 ገጽ ፡ 251)፡፡ አድ-ዳሩ-ል-ቁጥኒይ፣ ‹‹ይህ ትክክለኛ ሐዲሥ ነው፣ አስተላላፊዎቹም ሁሉም ተማኞች ናቸው፡፡›› ብለዋል (አስ-ሱነን  ቅጽ ፡ 2 ገጽ ፡ 46)፡፡ 

ግዴታ ከመሆን የሚያርቀው ደግሞ ከአቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ሰላቱን ላበላሸው ሰው ይህን እንዲል አላስተማሩትም፡፡ በአንጻሩ ወደመጽሐፉ የመክፈቻ ምዕራፍ ነበር ያመላከቱት፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (757) እንዲሁም ሙስሊም በቁጥር (397) ዘግበውታል፡፡ 

brightness_1 ከአል-ፋቲሐ ምዕራፍ በኋላ አንድ የቁርአን ምዕራፍ ማንበብ፡፡

በመጀመሪያዎቹ ሁለት ረከዐዎች ላይ ማንበቡ ነቢያዊ ፈለግ ነው የሚለው የአብዛኛዎቹ ዑለሞች -አላህ ይዝንላቸው- ሃሳብ ነው፡፡ አቢ ቀታዳህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹ነቢዩ -የአላህ እዝንታና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- በአዝ-ዙህር ሰላት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ረከዐዎች ላይ የአል-ፋቲሐን ምዕራፍና ሌሎች ሁለት ምዕራፎችን ያነቡ ነበር፡፡ የመጀመሪያውን ያስረዝሙ የነበር ሲሆን በሁለተኛው ላይ ያሳጥሩ ነበር፡፡›› ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (759) እንዲሁም ሙስሊም በቁጥር (451) ዘግበውታል፡፡ 

ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “የመጽሐፉን መክፈቻ ምዕራፍ ላላነበበ ሰላት የለውም፡፡” ማለታቸው የአል-ፋቲሐ ምዕራፍን ማንበብ ብቻ ከዘአል-ፋቲሐ ምዕራፍ በኋላ ለሚመጣው ምዕራፍ በቂው ነው ወይም ሌላ ምዕራፍ ሳያነቡ የአል-ፋቲሐ ምዕራፍን ብቻ ማንበብ ይቻላል የሚለውን ሃሳብ እንድንወስድ ያደርገናል፡፡ ድምጽ ይፋ ሆኖ በሚነበብባቸው ሰላቶች ተከታይ የሆነ ሰው ከአል-ፋተሐ በኋላ ያለውን  ምዕራፍን አያነብም፡፡ ዝም ብሎ የኢማሙን ንባብ ያዳምጣል፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (756) እንዲሁም ሙስሊም በቁጥር (394) ዘግበውታል፡፡  

ኢብን ቁዳመህ -አላህ ይዘንላቸው- እንዲህ ብለዋል፣ ‹‹በመጀመሪያዎቹ ሁለት ረከዐዎች ላይ ከአል-ፋቲሐ ምዕራፍ በኋላ አንድ የቁርኣን ምዕራፍን ማንበብ ነቢያዊ ፈለግ በመሆኑ ላይ በዑለሞች መካከል የሃሳብ ልዩነት መኖሩን አናውቅም፡፡›› አል-ሙግኒ  ቅጽ ፡ 1 ገጽ ፡ 568፡፡