brightness_1
ሰላምታ ማቅረብ ከነቢያዊ ፈለጎች ነው፡፡
ማስረጃዎቹ በጣም በርካታ ናቸው፡፡ ከእነር መካከል፡- አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “አንድ ሙስሊም በሙስሊም ላይ ያለው መብት ስድስት ነው፡፡” አሉ፡፡ ‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እነርሱ ምን ምን ናቸው? ተባሉ፡፡ እሳቸውም፣ “ስታገኘው ሰላም በለው፡፡ ከጠራህ ምላ ስጠው፡፡ ምክር ከጠየቀህ ምክር ለግሰው፡፡ አነጥሶ አላህን ካመሰገነ አላህ ይማርህ በለው፡፡ ከታመመ ጎብኘው፡፡ ከሞተ ተከተለው፡፡” አሉ፡፡ ሙስሊም በቁጥር (2162) ላይ ዘግበውታል፡፡
- ሰላምታን መመለስ (ምላሽ መስጠት) ግዴታ ነው፡፡ ለዚህም ማሰረጃው፡-
አላህ እንዲህ ብሏል፣ “በሰላምታም በተከበራችሁም ጊዜ ከርሷ ይበልጥ ባማረ (ሰላምታ) አክብሩ ወይም (እርሷኑ) መልሷት አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና፡፡” (አን-ነሳእ ፡ 86)፡፡
ግዴታ የመሆኑ መነሻ የሚከለክለው አንዳች ከልካይ ካልከለከለው ነው፡፡ ከዑለሞች መካከል አንዱ ብቻ ካልሆኑ በስተቀር ይህን ሃሳብ በጋራ ሃሳብነት ሁሉም አስተላልፈውታል፡፡ ከእነዚህ ዑለሞች መካከል፡- ኢብን ሐዝም፣ ኢብን ዐብዱ-ልበር ፣ ሸይኽ ተቂይዩ-ድዲንና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡ አዳቡ-ሽሸርዒየህ ቅጽ፡ 1 ገጽ ፡ 356፡፡ የአር-ሪሳለህ ድርጅት እትም፡፡
- በላጩ የሰላምታና የምላሸ ቃል እንዲሁም መሉ የሆነው የሰላምታ ቃል፡- “አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱ-ልላሂ ወበረካቱሁ፡፡” ነው፡፡ ይህ መልካሙና ሙሉው ሰላምታና፡፡
ኢብን አል-ቀይዪም -አላህ ይዘንላቸው- እንዲህ ብለዋል፣ ‹‹ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- አስተምህሯቸው ሰላምታን ‹‹ወበረካቱሁ›› እስከሚለው ድረስ ማጠናቀቅ ነው፡፡›› ዛዱ-ልሚዓድ ቅጽ ፡ 2 ገጽ ፡ 417፡፡
ሰላምታን ማሰራጨት፡- ነቢያዊ ፈለግ ሲሆን ትልቅ ትሩፋት ስላለውም ይበረታታል፡፡ አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! እስክታምኑ ድረስ ጀነት አትገቡም፡፡ እስከምትዋደዱ ድረስ አታምኑም፡፡ ከፈጸማችሁት የምትዋደዱበትን አንዳች ነገር ላመላክታችሁን? በመካከላችሁ ሰላምታን አሰራጩ፡፡”