brightness_1
አዛንን መከታተል
አዛንን የሚሰማ ሰው ሐይየ ዐለ-ስሰላህና ሐይየ ዐለ-ል-ፈላሕ ከሚለው በስተቀር ሙአዚኑ እንደሚለው ማለቱ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡ ሐይየ ዐለ-ስሰላህና ሐይየ ዐለ-ል-ፈላሕ ላይ ግን ‹‹ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢልላ ቢልላህ›› ይላል፡፡
ዐብዱላህ ኢብን ዐምር -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- “ሙአዚንን ከሰማችሁ እንደሚለው ዓይነት በሉ፡፡…” ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (384) ዘግበውታል፡፡ ከዑመር ኢብን አል-ኸጣብ (ረ.ዐ) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- “አንድ ሙአዚን ‹‹አላሁ አክበር አላሁ አክበር›› ሲል አንዳችሁ “ከልቡ አላሁ አክበር አላሁ አክበር” ካለ፣ (ሙአዚኑ) ‹‹አሽሀዱ አን ላኢላሀ ኢልለላህ›› ሲል (አንዳችሁ) ‹‹አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢልለላህ›› ካለ፣ (ሙአዚኑ) ‹‹አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉላህ›› ሲል (አንዳችሁ) ‹‹አሽሀዱ አንነ ሙሐመደን ረሱሉላህ›› ካለ፣ (ሙአዚኑ) ‹‹ሐይየ ዐለ-ስሰላህ›› ሲል (አንዳችሁ) “ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢልላ ቢልላህ” ካለ፣ (ሙአዚኑ) ‹‹ሐይየ ዐለል-ፈላሕ›› ሲል (አንዳችሁ) ‹‹ላ ሐውላ ወላ ቁውወተ ኢልላ ቢልላህ›› ካለ፣ (ሙአዚኑ) ‹‹አላሁ አክበር አላሁ አክበር›› ሲል (አንዳችሁ) ‹‹አላሁ አክበር አላሁ አክበር›› ካለ፣ (ሙአዚኑ) ‹‹ላ ኢላሀ ኢልለላህ ሲል (አንዳችሁ) ላ ኢላሀ ኢልለላህ›› ካለ ጀነት ገብቷል፡፡” ብለዋል፡፡ ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (385) ዘግበውታል፡፡
ለፈጅር ሰላት በማነሳሺያ ቃላት ወቅት አዛኑን የሚከታተል ሰው ሙአዚኑ እንደሚለው ‹‹አስ-ሰላቱ ኸይሩን ሚነ-ንነውም›› ይላል፡፡