brightness_1
ሽቶ መቀባት ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡
አነስ -አላህ መልካም ሠራዎቻቸውን ይውደዳቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ከምድራዊው ዓለም በእኔ ዘንድ ሰቶች፣ ሽቶ እጅግ የተወደዱ ተደርገውልኛል፡፡ የዓይን ማረፊያዬ በሰላት ውስጥ እንዲሁ ተደርጎልኛ፡፡” ብለዋል፡፡ አሕመድ በቁጥር (12293)፣ አን-ነሳኢይ በቁጥር (3940) የዘገቡት ሲሆን አል-አልባኒይ በሰሒሑ አን-ነሳኢይ ውስጥ ሐዲሡን ‹‹ሐሰኑን ሰሒሕ›› ብለዋል፡፡
ነገር ግን፣ “ከምድራዊው ዓለማችሁ በእኔ ዘንድ ሶስት ነገሮች የተወደዱ ተደርገውልኛል፡፡” የሚለው ዘገባ የሐዲሡ ደረጃ ደካማ ነው፡፡
ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ከእሳቸው ላይ መጥፎ ጠረን መኖርን ይጠሉ ነበር፡፡ ቡኻሪ ከዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- በዘገቡት ረዥም ሐዲሥ ውስጥ ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ከእሳቸው ላይ ሽታን ማግኘት ይበረታባቸው ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ ‹‹ሽታን ማግኘት ይበረታባቸው ነበር፡፡›› ማለት ጥሩ ያልሆነ ሽታን ማግኘት ማለት ነው፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (6972) ላይ ዘግበውታል፡፡
ሽቶን መመለስ ይጠላል
አነስ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ሽቶን አይመልሱም ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2582) ላይ ዘግበውታል፡፡