languageIcon
search
search
beforeFajronColorIcon / ገጽ/ ( ቁጥሯም 3 ሱንናዎች )
brightness_1 የቀደምት-ተምሳሌታዊ ትውልዶች ለነቢያዊ ፈለግ የነበራቸው ጉጉት ምሳሌዎች መካከል፡-

  1. ሙስሊም ትክክለኛ በሆነው የሐዲሥ ዘገባቸው ከአን-ኑዕማን ቢን ሳሊም እንደዘገቡት ዐምር ቢን አውስ -አላህ የሁለታቸውንም መልካም ሥራዎች ይውደድላቸው- እንዲህ ብለዋል፣ ‹‹ዐንበሳህ ቢን አቢ ሱፍያን እንዲህ አሉኝ፣ “ኡምሙ ሐቢበህ እንዲህ ሲሉ ሰምቻሉ፡-- የአላህ መልእክተኛ           -በእሳቸው ላይ የአላህ እዝነትና ሰላም ይሁን- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፣ ‹‹በቀንና በማታ አስራ ሁለት ረከዐዎችን የሰገደ፤ በእነርሱ ሰበብ ጀነት ውስጥ ቤት ይገነባለታል፡፡›› ብለዋል፡፡ ሙስሊም በሐዲሥ ቁጥር (1727) ዘግበውታል፡፡  ኡምሙ ሐቢባህ እንዲህ ብለዋል፤ ‹‹ይህን ከአላህ መልእክተኛ           -በእሳቸው ላይ የአላህ እዝነትና ሰላም ይሁን- ከሰማሁበት ጊዜ አንስቶ ፈጽሞ አልተውኳቸውም፡፡›› ዐንበሳህም እንዲህ ብለዋል፤ ‹‹ከኡምሙ ሐቢባህ ከሰማሁበት ጊዜ አንስቶ ፈጽሞ አልተውኳቸውም፡፡›› 

ዐምር ቢን አውስ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፤ ‹‹ከዐንበሳህ ከሰማሁበት ጊዜ አንስቶ ፈጽሞ አልተውኳቸውም፡፡››

አን-ኑዕማን ቢን ሳሊም ደግሞ እንዲህ ብለዋል፤ ‹‹ከዐምር ቢን አውስ ሰማሁበት ጊዜ አንስቶ ፈጽሞ አልተውኳቸውም፡፡››

2/ ከዐሊይ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንደዘገበው፤ ‹‹ከእለታት አንድ ቀን ፈጢማህ መጅ በእጇ ላይ የሚያስከትለውን ችግር አስመልክታ ቅሬታ አቀረበች፡፡ ወደነቢዩ -በእሳቸው ላይ የአላህ እዝነትና ሰላም ይሁን- ዘንድ የጦር ምርኮኛች መጡ፡፡ እሷ ወደእሳቸው ዘንድ ሄደች፡፡ አላገኘቻቸውም፡፡ ዓኢሻህን አገኘቻትና ቅሬታውን ነገረቻት፡፡ ነቢዩ -በእሳቸው ላይ የአላህ እዝነትና ሰላም ይሁን- ወደቤታቸው ሲመጡ ፈጢማህ ወደእሷ ዘንድ እንደመጣች ዓኢሻ ነገረቻቸው፡፡ እሳቸወም ወደኛ ዘንድ መጡ፡፡ በእርግጥ ለመተኛት መኝታችንን ይዘናል፡፡ ካለንበት ልንነሳ ስንል፣ ነቢዩ   -በእሳቸው ላይ የአላህ እዝነትና ሰላም ይሁን- ‹‹በቦታችሁ ላይ ሁኑ›› አሉን፡፡ የእግራቸውን ቅዝቃዜ ደረቴ ላይ እስካዳምጥ ድረስ መጥተው በመካከላችን  ተቀመጡና፤ ‹‹ከጠየቃችሁት ነገር የተሸለን ነገር ላስተምራችሁን? ለመተኛት መኝታቸሁን ስትይዙ ሰላሳ አራት ጊዜ ተክቢራ ታደርጋላችሁ፡፡ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ተስቢሕ ታደርጋላችሁ፡፡ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አል-ሐምዱሊላህ ትላላችሁ፡፡ ይህ ለናንተ ካገልጋይ የተሻለ ነው፡፡›› አሉ፡፡›› ብለዋል፡፡ ቡኻሪ በሐዲሥ ቀጥር (3705) ሙስሊም ደግሞ በሐዲሥ ቁጥር (2727) ዘግበውታል፡፡     

በሌላ ዘገባ ዐሊይ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ፤ ‹‹ይህን ከነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ከሰማሁ አንስቶ አልተውኩትም፡፡›› አሉ፡፡ ‹‹የሲፍፈይ ሌሊት ላይም ቢሆን እንኳ?›› ተባሉ፡፡ እቸውም፤‹‹የሲፍፈይ ሌሊት ላይም ቢሆን እንኳ›› አሉ፡፡ ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (5362) ሙስሊም ደግሞ በሐዲሥ ቁጥር ዘገባ (2727) ዘግበውታል፡፡

እንደሚታወቀው የሲፍፈይን ሌሊት ጦርነት የተካሄደበት ሌሊት ነበር፡፡ በዚህ ጦርነት ላይም ዐሊይ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ጦር ማሪ ነበሩ፡፡ ይሁን ቢሆን ከዚህ ዓይነቱ ነቢያፊ ፈለግ ጦርነቱ እንዲዘናጉ አላደረጋቸውም፡፡

3/ ኢብን ዑመር -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- አስክሬን ላይ ይሰግዱ ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ሁኔታ ነቢያዊ ፈለጉን ማሟያ ነው ብለው ስለሚጠረጥሩ ነበር፡፡ ይን የሚያደርጉት አስክሬንን እሰከሚቀበር ድረስ የመሸኘትን ትሩፋት አስመልከቶ የተነገረውን የነቢያዊ አስተምህሮ ፈጽሞ ሰለማያውቁ ነበር፡፡ ይህን አስመልከቶ በአቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- የተላለፈው ነቢያዊ አስትምህሮ ሲደርሳቸው ነቢያዊ ፈለጉን በመተዋቸው በጣም ተጸጸቱ፡፡ ታዲያማ ምን እንዳሉ ታውቃላችሁ? እሰኪ አስተውሉ፡፡

በእፍኛቸው ይዘዋቸው በነበረው ጠጠሮች መሬቱን መቱና፣ ‹‹በርግጥ በበርካታ ድልቦች ላይ ተዘናግተናል፡፡›› አሉ፡፡ ቡኻሪ ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (1324) እንዲሁም ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (945) ላይ ዘግበውታል፡፡   

ኢማም አን-ነወዊይ -አላህ ይዘንላቸው-፤ ‹‹ሰሓቦች ትእዛዛት ሲደርሷቸው ለመተግበር ምን ያህል ፍላጎት እንደነበራቸውና ከተእዛዛቱ አንዱ ሲያመልጣቸው ምን ያህል እንደሚያዝኑ እንዲሁም ሁኔታውን አለማወቃቸውን ሲረዱ ሁኔታቸው ምን ያህል እንደሚገዝፍ በዚህ ክስተት ውስጥ እንረዳለን፡፡›› ብለዋል፡፡

brightness_1 ነቢያዊ ፈለግን በመከተል ካለው ትሩፋቶች መካከል፡-

ውድ አንባቢያን ሆይ! ነቢያዊ ፈለግን መከተል በርካታ ትሩፋቶች አለው፡፡ ከእርሱም መካከል፡-

1/የውዴታን ደረጃ ያቀዳጃል፡፡ ግዴታ ባልሆኑ ተግባራት እጅጉን ወደላቀውና ልእልና ወደተገባው  አላህ ዘንድ መቃረብ እጅግ የላቀውና ልእልና የተገባው አላህ ለባሪያው የሚሰጠውን ውዴታ ያስገኛል፡፡

ኢብን አል-ቀይዪም -አላህ ይዘንላቸው- እንዲህ ብለዋል፤ ‹‹ በይፋም ሆነ በድብቅ በእሱ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑትን ነቢይ እስካልተከተልክ፣ መልእክታቸውን እውነት እስካላላልክ፣ ጥሪያቸውንና ፈለጋቸውን እስካልተከተልክ፣ በፍርዳቸው የሌሎችን ፍርዶች፣ በውዴታቸው የሌሎች ፍጡራንን ውዴታ እንዲሁም ትእዛዞቻቸውን በመታዘዝ ለሌሎች ያለህን መታዘዝ  እንካላጠፋህ ድረስ አላህ አይወድህም፡፡ ይህ ካልሆነ በከንቱ አትድከም፡፡ ወዳሻህ ስፍራም ተመለስ፡፡ በአንዳች ነገር ላይ ስላልሆንክ ብርሃንን ፈልግ፡፡›› መዳሪጁ-ስሳሊከይን ቅጽ፡ 3 ገጽ ፡ 37ን ይመልከቱ፡፡

2/ የላቀው አላህ ለባሪያው የሚሰጠውን እገዛ ያቀዳጃል፡፡ ነቢያዊ ፈለጎችን የሚከተልን ሰው አላህ መልካም ነገሮች ይገጥመዋል፡፡ ጌታው ከሚውደው ነገር ውጭ ከንቱና ውድቅ የሆኑ ተግባራት ከእሱ ዘንድ አይፈልቁም፡፡ ምክንያቱም ይህ ዓይቱ ሰው የአላህን ውዴታ በርግት ካገኘ የአላህን እርዳታንም እንዲሁ አግኝቷል፡፡

3/ ተወዳጅነትን የተቀዳጀ ሰው የሚያደርገው ዱዓእ ተቀባይነት ለው ለመሆኑ ዋስትና አለው፡፡ ግዴታ ባልሆኑ ተግባራት ወደላቀውና ልእልና ወደተገባው  አላህ ዘንድ የተቃርበ የአላህን ውዴታ ያገኛል፡፡ የአላህን ውዴታ ያገኝ ሰው ደግሞ የዱዓውን ተቀባይነት ያገኛል፡፡

እነዚህን ትሩፋቶች ሶሰት ሐዲሦች ያረጋግጣሉ፡-

አቡ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸወን ይቀበላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ - የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- እንዲህ ብለዋል፤ ‹‹በርግጥ አላህ አንዲህ ብሏል፣- “ለእኔ ባላንጣ ያደረገን ሰው በርግጥ በጦርነት እጋፈጠዋልሁ፡፡ ባሪያዬ እኔ ግዴታ ካደረግኩበት ነገር ውጭ በእኔ ዘንድ ተወዳጅ በሆነ ነገር አይቃረብም፡፡ ባሪያዬ እከምወደው ድረስ ግዴታ ባልሆኑ ተግባራት ወደኔ ከመቃረብ አይታክትም፡፡ ከወደድኩት የሚሰማበትን መስሚያ ጆሮ፣ የሚያይበትን ዓይን፣ የሚዳስስበትን እጅ፣ የሚራመድበትን እግር እሆንለታለሁ፡፡ ከጠየቀኝ በርግጥ እሰጠዋለሁ፡፡ ጥበቃ ከጠየቀኝም በርግጥ እጠብቀዋለሁ፡፡ እኔ ክፉውን ነገር እንደምጠላለትና ሞትን ከሚጠላው የሙእሚን ነፍስ ይበልጥ  ከምፈጽመው አንዳች ነገር ወደኋላ አልልምም፡፡”›› ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (6502) ላይ ሐዲሡን ዘግበውታል፡፡ 

4/ ግዴታ የሆኑ ተግባራት ሲጓደሉና ያልተሟሉ ሲሆኑ ግዴታ ያልሆኑ ተግባራት እነዚህን ያልተሟሉ ግዴታ የሆኑ ተግባራትን ይሞላሉ፡፡

ይህንንም የሚያረጋግጥልን ማረስጃ

አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- እንዲህ ማለታቸውን ሰምቻለሁ ብለዋል፣‹‹በትንሳኤ እለት አንድ የአላህ ባሪያ ከሥራዎቹ መካከል  በቅድሚያ የሚተሳሰብበት ነገር ሰግዴቱ ነው፡፡ ስግደቱ ከተስተካከለች በርግጥ ነጻ ወጥቷል፡፡ ድልም ተቀዳጅቷል፡፡ ስግደቱ ከተበላሸችበት በርግጥ ከንቱ ሆነ ከሰረም፡፡ ግዴታ ከሆነበት ተግባሩ አንዳች ነገር ከጎደለ እጅግ የላቀውና ልእልና የተገባው አላህ ፤ “ባረያዬ በፈቀደኝነት የፈጸመው ተግባር አለን? እስኪ ተመልከቱ፡፡” ይላል፡፡ በፈቀደኝነት በሰራው ሥራ የጎደለው ይሟላለታል፡፡ ከዚያ ቀሪዎቹ ሥራዎቹ በዚያ ሁኔታ ላይ ይሆናሉ፡፡›› አቡ ዳዉድ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (864) እንዲሁም አት-ቲርሚዚይ በቁጥር (413)  ሐዲሡን የዘገቡት ሲሆን አል-አልባኒ በትክክለኛ የሐዲሥ ዘገባ ድርሳናቸው ላይ ትክክለኛነቱን አጽድቀዋል፡፡ (ሰሒሑ-ል-ጃሚዕ ቅጽ ፡ 1 ገጽ፡ 405)