brightness_1
أَمْسَيْنَا عَلَى فِطْرَةِ الْإِسْلَامِ، وَكَلِمَةِ الْإِخْلَاصِ، وَدِينِ نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ - صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ - وَمِلَّةِ أَبِينَا إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا, وَمَا كَانَ مِنْ الْمُشْرِكِينَ
‹‹የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ሲያነጉ፣ “አስበሕና ዐላ ፊጥረቲ-ልኢስላም፣ ወከሊመቲ-ልኢኽላስ፣ ወዲኒ ነቢይዪና ሙሐምመዲን -ሰልለላሁ ዐለይሂ ወሰልለም- ወሚልለቲ አቢይና ኢብራሂይመ ሐኒይፈን ወማ ካነ ሚነ-ልሙሽሪኪይን፡፡ /በኢስላም ተፈጥሮ ላይ፣ በቅንነት ቃል፣ በነብያችን ሙሐመድ -የአላህ እዝንትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ዲን ላይና በቀጥተኛው የአባታችን መንገድ ላይ አነጋን፡፡ በእርግጥ እሳቸው አጋሪ አልነበሩም፣” ይሉ ነበር፡፡›› ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (21144፣ 15365) ላይ ዘግበውታል፡፡ ሲያመሹም፣ “አምሰይና ዐላ ፊጥረቲል-ኢስላም…/በኢስላም ተፈጥሮ ላይ አመሸን…/” ይሉ ነበር፡፡ የሐዲሡን የዘገባ ሰነድ ትክክለኛነት ኢብን ባዝ -አላህ ይዘንላቸው- አረጋግጠዋል፡፡
.......