ማስረጃዎቹ በጣም በርካታ ናቸው፡፡ ከእነር መካከል፡- አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “አንድ ሙስሊም በሙስሊም ላይ ያለው መብት ስድስት ነው፡፡” አሉ፡፡ ‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እነርሱ ምን ምን ናቸው? ተባሉ፡፡ እሳቸውም፣ “ስታገኘው ሰላም በለው፡፡ ከጠራህ ምላ ስጠው፡፡ ምክር ከጠየቀህ ምክር ለግሰው፡፡ አነጥሶ አላህን ካመሰገነ አላህ ይማርህ በለው፡፡ ከታመመ ጎብኘው፡፡ ከሞተ ተከተለው፡፡” አሉ፡፡ ሙስሊም በቁጥር (2162) ላይ ዘግበውታል፡፡
- ሰላምታን መመለስ (ምላሽ መስጠት) ግዴታ ነው፡፡ ለዚህም ማሰረጃው፡-
አላህ እንዲህ ብሏል፣ “በሰላምታም በተከበራችሁም ጊዜ ከርሷ ይበልጥ ባማረ (ሰላምታ) አክብሩ ወይም (እርሷኑ) መልሷት አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና፡፡” (አን-ነሳእ ፡ 86)፡፡
ግዴታ የመሆኑ መነሻ የሚከለክለው አንዳች ከልካይ ካልከለከለው ነው፡፡ ከዑለሞች መካከል አንዱ ብቻ ካልሆኑ በስተቀር ይህን ሃሳብ በጋራ ሃሳብነት ሁሉም አስተላልፈውታል፡፡ ከእነዚህ ዑለሞች መካከል፡- ኢብን ሐዝም፣ ኢብን ዐብዱ-ልበር ፣ ሸይኽ ተቂይዩ-ድዲንና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡ አዳቡ-ሽሸርዒየህ ቅጽ፡ 1 ገጽ ፡ 356፡፡ የአር-ሪሳለህ ድርጅት እትም፡፡
- በላጩ የሰላምታና የምላሸ ቃል እንዲሁም መሉ የሆነው የሰላምታ ቃል፡- “አስሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱ-ልላሂ ወበረካቱሁ፡፡” ነው፡፡ ይህ መልካሙና ሙሉው ሰላምታና፡፡
ኢብን አል-ቀይዪም -አላህ ይዘንላቸው- እንዲህ ብለዋል፣ ‹‹ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- አስተምህሯቸው ሰላምታን ‹‹ወበረካቱሁ›› እስከሚለው ድረስ ማጠናቀቅ ነው፡፡›› ዛዱ-ልሚዓድ ቅጽ ፡ 2 ገጽ ፡ 417፡፡
ሰላምታን ማሰራጨት፡- ነቢያዊ ፈለግ ሲሆን ትልቅ ትሩፋት ስላለውም ይበረታታል፡፡ አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ! እስክታምኑ ድረስ ጀነት አትገቡም፡፡ እስከምትዋደዱ ድረስ አታምኑም፡፡ ከፈጸማችሁት የምትዋደዱበትን አንዳች ነገር ላመላክታችሁን? በመካከላችሁ ሰላምታን አሰራጩ፡፡”
ለመጀመሪያ ጊዜ ሰላምታ ሲያቀርብለት ሙስሊም የሆነው ሰው መስማቱን ከተጠራጠረ ሁለት ጊዜ መደጋገሙ የተወደደ ነው፡፡ ካልሰማም ሶሰት ጊዜ፡፡ ብዙ ሰዎች የተሰበሰቡበት ቦታ ሲገባም እንዲሁ ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ትልቅ ስብሰባ መካከል ሲገባ ሰዎቹ በርካታ ከሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰላምታ ሲያቀርብ በመጀመሪያው ረድፍ ካሉት በስተቀር ሌሎች አይሰሙትም፡፡ ስለዚህ በስብሰባው ውስጥ ያሉትን ሁሉ ለማጠቃለል ሶስት ጊዜ መደጋገም ያስፈልጋል፡፡
ለዚህ ማሰረጃው፡- አነስ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ‹‹ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- አንዳች ቃል ከተናገሩ ሰዎችን ከእሳቸው እስኪረዷቸው ድረስ ሶስት ጊዜ ይደጋግሙት ነበር፡፡ ወደሰዎች ስብስብ ሲመጡ ሰላም ይሏቸዋል፡፡ ሶሰት ጊዜም ሰላም ይሏቸዋል፡፡›› ብለዋል፡፡ ቡኻሪ በቁጥር (95) ላይ ዘግበውታል፡፡
ከአነስ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ሐዲሥ ችግር እስካስገደደ ድረስ አንድ ቃል መረዳትን እስከያገኝ ድረስ ሶሰት ጊዜ እንደሚደጋገመው ሰላምታን ሶስት ጊዜ የመደጋገምን ነቢያዊ ፈለግነት ጭብጥ መውሰድ እንችላለን፡፡
አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ጋላቢ የሆነ በእግረኛ ላይ ፣ እግረኛ የሆነ በተቀመጠ ሰው ላይ፣ ጥቂቶች በብዙዎች ላይሰላምታን ያቅርብ፡፡” ብለዋል፡፡ ቡኻሪ በቁጥር (2633)፣ ሙስሊም በቁጥር (2160) ላይ የዘገቡት ሲሆን በቡኻሪ ሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ፣ “ትንሽ ልጅ ለትልቅ ሰው፣ አላፊ በተቀማጭ፣ “ጥቂቶች በብዙዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ፡፡” የሚል ተዘግቧል፡፡ ቡኻሪ በቁጥር (6234) ላይ ዘግበውታል፡፡
ሰላምታን በቅድሚያ ማቅረብ እዚህ ላይ ለመቃረን ሳይሆን ይህንኑም መተግበር ምንም ችግር የለውም፡፡ ይሁን እንጂ ተቃራኒው ማለትም ትልቁ ለትንሹ፣ እግረኛው በጋላቢው ወ.ዘ.ተ በመሳሰሉት ሁኔታ መተግበር ቅደሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው፡፡
አነስ ኢብን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹ከአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ጋር እየሄድኩ ነበር፡፡ በሕጻናት አጠገብን አለፍን፡፡ እሳቸው ሰላምታ አቀረቡላቸው፡፡›› ብለዋል፡፡ ቡኻሪ በቁጥር (6247)፣ ሙሰሊም በቁጥር (2168) ላይ ዘግበውታል፡፡
ይህ ለሕጻናት ሰላምታ ማቅረብ ነፍስ መተናነስን እንድትለምድ ሃላፊነት ማሸከምና ሕጻናት ይህን እሴት እንዲላመዱና ሕያው እንዲያደርጉ ለማስቻል የሚረዳ ነው፡፡
ይህ ተግባር በሁሉም የሰላምታ ዓይነቶች ላይ ይካተታል፡፡ ይህም ግለሰቡ ጥርሱን ከፋቀ በኋላ ነው፡፡ ምክንያቱም ወደቤት ሲገቡ ጥርሰን መፋቅ (መፋቂያ መጠቀም) ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡ ይህ መፋቂያ ነቢያዊ ፈለግ መሆኑንን የሚያረጋጠው አራተኛው ስፍራ ነው፡፡ ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ ላይ ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹ ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ቤታቸው ሲገቡ ጥርሳቸውን መፋቅ ይጀምራሉ፡፡›› ብለዋል፡፡ ሙስሊም በቁጥር (253) ላይ ዘግበውታል፡፡ ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ቤታቸው ሲገቡ ጥርሳቸውን በመፋቅ ይጀምሩ ነበር፡፡ ከዚያ ለቤተሰቦቻቸው ሰላምታ ያቀርቡ ነበር፡፡ የተወሰኑ ዑለሞች፣ ‹‹ወደቤት ስትገባ ሰላምታ ማቅረብህና የትኛውም ቤት አንድም ሰው ባይኖርም ሰላምታ ማቅረብህ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ ይህም አላህ እንዲህ በማለቱ ነው፣ “ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ ከአላህ ዘንድ የኾነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ፤ እንደዚህ አላህ አንቀጾችን ለናንተ ያብራራል፤ ልታውቁ ይከጅላልና፡፡” (አን-ኑር ፡ 60)፡፡
ኢብን ሐጀር -አላህ ይዘንላቸው-፣ ‹‹በራስ ላይ ሰላምታን ማቅረብ ሰላምታን በማሰራጨት ሥር ይጠቃለላል፡፡ ይህም አንድም ሰው በሌለበት ሥፍራ የገባም ቢሆን ማለት ነው፡፡ ይህም አላህ እጅግ የላቀው ጌታ፣ “ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ ከአላህ ዘንድ የኾነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ፤” (አን-ኑር ፡ 60) ስላለ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ አል-ፈትሕ ሰላምታን በማሰራጨት ምዕራፍ ሥር ሐዲሥ ቁጥር (6235)ን ይመልከቱ፡፡
የመጀመሪያው፡- ሌሊት ቢሆንም -እጅግ የላቀውን- አላህን ስም ማውሳት
ጃቢር ኢብን ዐብዲላህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውነ ይውደድላቸው- የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ ይውደድላቸው- ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “አንድ ሰው ወደቤቱ ሲገባ በምግባቱና በምግቡ ላይ የአላህን ስም ካወሳ ሸይጣን፡- ማደሪያና እራት የላችሁም ይላል፡፡ ሰውዬው ሲገባ በመግባቱ ላይ የአላህን ስም ካላወሳ ሸይጣን፡- ማደሪያ አገኛችሁ፡፡ ” በምግቡ ላይ የአላህን ስም ካላወሳ ሸይጣን፡- ማደሪያና እራት አገኛችሁ፡፡ ይላል፡፡” ሲሉ መስማታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ሐዲሡን ሙስሊም በሐዲሥ ቁጥር (2018) ላይ ዘግበውታል፡፡
ሁለተኛው፡- ከዚህ በላይ በዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ባወሩት ሐዲሥ መሰረት ጥርስን መፋቅ (መፋቂያ መጠቀም)፡፡
ሶስተኛው፡- ለቤተሰቡ ሰላምታ ማቅረብ፡፡
ምክንያቱም አል-ሚቅዳድ ኢብን አል-አስወድ -አላህ መልካም ስራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ባስተላለፉት ሐዲሥ ላይ እንደሰፈረው ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- እንዲህ ነበር ይፈጽሙ የነበሩት፡፡ አል-ሚቅዳድ በዚህ ሐዲሥ ላይ፣ ‹‹… ወተት እናሳልብና ሁሉም የየድርሻውን ይጠጣል፡፡ ለነቢዩም -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- የድርሻቸውን እንሰጣቸው ነበር፡፡ ከሌሊቱ ባንድ ወቅት ላይ ይመጡና የነቃ ሰው የሚሰማውንና የተኛ ሰውን የማያነቃ ሰላምታን ሰላም ይሉ ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ ሙስሊም በቁጥር (2055) ላይ ዘግበውታል፡፡
አንድ ሰው፣ ‹‹እከሌን ሰላም በልልኝ፡፡›› እንደሚለው ዓይነት ሰላምታን ማድረስ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡
ለዚህ ማስረጃው፡- ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “በርግጥ ጅብሪል ባንቺ ላይ ሰላምታ ያቀርባል፡፡” አሏቸው፡፡ እሳቸውም፣ ‹‹በእሱ ላይ የአላህ ሰላምታና እዝነት ይሁን›› አልኳቸው፡፡›› ብለዋል፡፡ ቡኻሪ በቁጥር (3217)፣ ሙስሊም በቁጥር (2447) ላይ ዘግበውታል፡፡
ከዚህ የዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-ሐዲሥ ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- የጅብሪልን -የአላህ ሰላምታ በእሱ ላይ ይሁን- ሰላምታን ለዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳደረሱላቸው ሰላምታን ወደባለቤቱ ማድረስ ነቢያዊ ፈለግ እንደሆነ እንረዳለን፡፡
አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “አንዳችሁ ስብሰባን ሲያጠናቅቅ ሰላምታ ያቅርብ፡፡ ለመነሳት ሲፈልግ ሰላምታ ያቅርብ፡፡ የመጀመሪያዋ ከመጨረሻዋ ይበልጥ መብት ያላት አይደለችም፡፡” ብለዋል፡፡ አሕመድ በቁጥር (9664)፣ አቡ ዳዉድ በቁጥር (5208)፣ አት-ቲርሚዚይ በቁጥር (2706) የዘገቡት ሲሆን አል-አልባኒም ትክክለኛቱን አረጋግጠዋል፡፡ ሰሒሑ-ልጃሚዕ ቅጽ ፡ 1 ገጽ ፡ 132፡፡
አቢ ዘር -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ከመልካም ነገር አንዳች ነገር አታሳንስ፡፡ ወንድምህን በመልካም ገጽታ መገናኘትን ቢሆን፡፡” አሉኝ፡፡›› ብለዋል፡፡ ሙስሊም በቁጥር (2626) ላይ ዘግበውታል፡፡ አት-ቲርሚዚይ ከአቢ ዘር -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “በወንደምህ ፊት ፈገግ ማለትህ ላንተ ሰደቃህ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ አት-ቲርሚዚይ በቁጥር (1956) ላይ ሲዘግቡት አል-አልባኒም ትክክለኛቱን አረጋግጠዋል፡፡ አስ-ሰሒሐህ 572 ፡፡
በመገኛኘት ወቅትም ሆነ አብረው በሚቀመጡበት ወቅት ወይም በማንኛውም አጋጣሚ መልካም ንግግር ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰደቃህ (ምጽዋት) ነውና፡፡
ለዚህ ማስረጃው፡- አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “መልካም ንግግር ሰደቃህ (ምጽዋት) ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ቡኻሪ በቁጥር (2989)፣ ሙስሊም በቁጥር (1009) ላይ ዘግበውታል፡፡
በበርካታ ሰዎች አንደበት ላይ አብዛኛውን ጊዜ መልካም ንግግር አይጠፋም፡፡ ይሁን እንጂ ምንዳን ቢያስቡ ኖሮ በርካታ ምንዳዎችን ከመጎጸፋቸው ባሸገር እጅግ በርካታ ምጽዋትን (ሰደቃዎችን) ባካበቱ ነበር፡፡
ሸይኻችን ኢብን ዑሠይሚን -አላህ ይዘንላቸው-፣ ‹‹መልካም ንግግር ማለት ለአንድ ሰው፣ ‹እንዴት ነህ? ጤናህ እንዴት ነው? ወንድሞችህ እንዴት ናቸው?
ቤተሰቦችችህ እንዴት ናቸው? እና ወ.ዘ.ተ ማለትህ ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ቃላት ወዳጅህ ደስታን ያሰርጻሉ፡፡ እያንዳንዱ መልካም ቃል አላህ ዘንድ ምጽዋትህ (ሰደቃህ)፣ ምንዳህና ሽልማትህ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ ሸርሑ ሪያዱ-ስሳሊሒን ቅጽ ፡ 2 ገጽ ፡ 996 በመገናኘት ወቅት መልካም ንግግርና መልካም ገጽታ የተወደደ ሰእለመሆኑ ምዕራፍ፡፡
የመሰብሰብን ትሩፋቶች የሚያመለክቱ በርካታ ሐዲሦች ተዘግበዋል፡፡ ከእነዚህ ሐዲሦች መካከልም አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ለአላህ እሱ የሚወሳበትን ስፍራ የሚፈልጉ የሆኑ፣ የተከበሩና ተጓዥ የሆኑ መላእክት አሉት፡፡ ዚክር ያለበትን ስብሰባ ካገኙ ዚክር ከሚያደርጉት ሰዎች ጋር አብረው ይቀመጣሉ፡፡ አንዳቸው አንዳቸውን በክንፎቻቸው ያቅፋሉ፡፡ በመካከላቸው በምድራዊ ሰማይ መካከል ያለውን ስፍራ እስከሚሞሉ ድረስ በክንፎቻቸው ያካብቧቸዋል፡፡” ቡኻሪ በቁጥር (6408)፣ ሙስሊም በቁጥር (2689) ላይ ዘግበውታል፡፡
አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “አንድ ባልቱ የበዛበት ስብሰባ ውስጥ ተቀምጦ (ታድሞ) ከዚያ መቀመጫው ሳይነሳ በፊት፡- ሱብሓነከ-ልላሁምመ ወቢሐምዲከ አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢልላ አመተ አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይክ፡፡ /በምስጋናህም ከከንቱና ወድቅ ከሆነው ንግግር በእጅጉ የጠራህ የሆነው አላህ ሆይ! ከአንተ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፣ ምሕረት እጠይቃለሁ፡፡ ወዳንተም በንሰሐ እመለሳለሁ፡፡/ ካለ በዚያ መቀመጫው ሳለ ምሕረት ተደርጎለታል፡፡” አት-ቲርሚዘይ በቁጥር (3433) የዘገቡት ሲሆን ኢብን ሐጀር -አላህ ይዘንላቸው- በአል-ፈትሕ የመጨረሻው ማብራሪያ ላይ፣ ‹‹የሰገባ ሰነዱ ጠንካራ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ አል-አልባኒይ ትክክለኛነቱን አረጋግጠዋል፡፡ ሰሒሑ-ልጃሚዕ ቅጽ ፡ 2 ገጽ ፡ 1065፡፡