languageIcon
አማርኛ
አማርኛ
العربية
Azeri
বাংলা
Bosanski
Deutsch
English
Español
Filipino
فارسي
Français
(Hausa) هَوُسَ
हिन्दी
Indonesia
italiano
Қазақ тілі
தமிழ்
كوردی
नेपाली
Português
Pусский
සිංහල‎
Gjuha shqipe
Kiswahili
ภาษาไทย
Türkçe
Українська
اردو
Yorùbá
中文
search
search
ወደቤት ሲገቡ ሰላምታ ማቅረብ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡

ይህ ተግባር በሁሉም የሰላምታ ዓይነቶች ላይ ይካተታል፡፡ ይህም  ግለሰቡ ጥርሱን ከፋቀ በኋላ ነው፡፡ ምክንያቱም ወደቤት ሲገቡ ጥርሰን መፋቅ (መፋቂያ መጠቀም) ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡ ይህ መፋቂያ ነቢያዊ ፈለግ መሆኑንን የሚያረጋጠው አራተኛው ስፍራ ነው፡፡ ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ ላይ ዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹ ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ቤታቸው ሲገቡ ጥርሳቸውን መፋቅ ይጀምራሉ፡፡›› ብለዋል፡፡ ሙስሊም በቁጥር (253) ላይ ዘግበውታል፡፡ ነቢዩ    -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ቤታቸው ሲገቡ ጥርሳቸውን በመፋቅ ይጀምሩ ነበር፡፡ ከዚያ ለቤተሰቦቻቸው ሰላምታ ያቀርቡ ነበር፡፡ የተወሰኑ ዑለሞች፣ ‹‹ወደቤት ስትገባ ሰላምታ ማቅረብህና የትኛውም ቤት አንድም ሰው ባይኖርም ሰላምታ ማቅረብህ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ ይህም አላህ እንዲህ በማለቱ ነው፣ “ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ ከአላህ ዘንድ የኾነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ፤ እንደዚህ አላህ አንቀጾችን ለናንተ ያብራራል፤ ልታውቁ ይከጅላልና፡፡” (አን-ኑር ፡ 60)፡፡

ኢብን ሐጀር -አላህ ይዘንላቸው-፣ ‹‹በራስ ላይ ሰላምታን ማቅረብ ሰላምታን በማሰራጨት ሥር ይጠቃለላል፡፡ ይህም አንድም ሰው በሌለበት ሥፍራ የገባም ቢሆን ማለት ነው፡፡ ይህም አላህ እጅግ የላቀው ጌታ፣ “ቤቶችንም በገባችሁ ጊዜ ከአላህ ዘንድ የኾነችን የተባረከች መልካም ሰላምታ በነፍሶቻችሁ ላይ ሰላም በሉ፤” (አን-ኑር ፡ 60) ስላለ ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ አል-ፈትሕ ሰላምታን በማሰራጨት ምዕራፍ ሥር ሐዲሥ ቁጥር (6235)ን ይመልከቱ፡፡

  1. ፋይዳ፡- ከዚህ በላይ ከሰፈረው ወደቤት ሲገባ ሶስት ተግባራትን መፈጸም ነቢያዊ ተግባር ነው፡፡ እነርሱም፡-

የመጀመሪያው፡- ሌሊት ቢሆንም -እጅግ የላቀውን- አላህን ስም ማውሳት

ጃቢር ኢብን ዐብዲላህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውነ ይውደድላቸው- የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ ይውደድላቸው- ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “አንድ ሰው ወደቤቱ ሲገባ በምግባቱና በምግቡ ላይ የአላህን ስም ካወሳ ሸይጣን፡- ማደሪያና እራት የላችሁም ይላል፡፡ ሰውዬው ሲገባ በመግባቱ ላይ የአላህን ስም ካላወሳ ሸይጣን፡- ማደሪያ አገኛችሁ፡፡ በምግቡ ላይ የአላህን ስም ካላወሳ ሸይጣን፡- ማደሪያና እራት አገኛችሁ፡፡ ይላል፡፡” ሲሉ መስማታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ሐዲሡን ሙስሊም በሐዲሥ ቁጥር (2018) ላይ ዘግበውታል፡፡

ሁለተኛው፡- ከዚህ በላይ በዓኢሻህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ባወሩት ሐዲሥ መሰረት ጥርስን መፋቅ    (መፋቂያ መጠቀም)፡፡

ሶስተኛው፡- ለቤተሰቡ ሰላምታ ማቅረብ፡፡

 
Simple Audio Player
 
facebook googleplus twitter