ነቢያዊ ፈለግን በመከተል ካለው ትሩፋቶች መካከል፡-
ውድ አንባቢያን ሆይ! ነቢያዊ ፈለግን መከተል በርካታ ትሩፋቶች አለው፡፡ ከእርሱም መካከል፡-
1/የውዴታን ደረጃ ያቀዳጃል፡፡ ግዴታ ባልሆኑ ተግባራት እጅጉን ወደላቀውና ልእልና ወደተገባው አላህ ዘንድ መቃረብ እጅግ የላቀውና ልእልና የተገባው አላህ ለባሪያው የሚሰጠውን ውዴታ ያስገኛል፡፡
ኢብን አል-ቀይዪም -አላህ ይዘንላቸው- እንዲህ ብለዋል፤ ‹‹ በይፋም ሆነ በድብቅ በእሱ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑትን ነቢይ እስካልተከተልክ፣ መልእክታቸውን እውነት እስካላላልክ፣ ጥሪያቸውንና ፈለጋቸውን እስካልተከተልክ፣ በፍርዳቸው የሌሎችን ፍርዶች፣ በውዴታቸው የሌሎች ፍጡራንን ውዴታ እንዲሁም ትእዛዞቻቸውን በመታዘዝ ለሌሎች ያለህን መታዘዝ እንካላጠፋህ ድረስ አላህ አይወድህም፡፡ ይህ ካልሆነ በከንቱ አትድከም፡፡ ወዳሻህ ስፍራም ተመለስ፡፡ በአንዳች ነገር ላይ ስላልሆንክ ብርሃንን ፈልግ፡፡›› መዳሪጁ-ስሳሊከይን ቅጽ፡ 3 ገጽ ፡ 37ን ይመልከቱ፡፡
2/ የላቀው አላህ ለባሪያው የሚሰጠውን እገዛ ያቀዳጃል፡፡ ነቢያዊ ፈለጎችን የሚከተልን ሰው አላህ መልካም ነገሮች ይገጥመዋል፡፡ ጌታው ከሚውደው ነገር ውጭ ከንቱና ውድቅ የሆኑ ተግባራት ከእሱ ዘንድ አይፈልቁም፡፡ ምክንያቱም ይህ ዓይቱ ሰው የአላህን ውዴታ በርግት ካገኘ የአላህን እርዳታንም እንዲሁ አግኝቷል፡፡
3/ ተወዳጅነትን የተቀዳጀ ሰው የሚያደርገው ዱዓእ ተቀባይነት ለው ለመሆኑ ዋስትና አለው፡፡ ግዴታ ባልሆኑ ተግባራት ወደላቀውና ልእልና ወደተገባው አላህ ዘንድ የተቃርበ የአላህን ውዴታ ያገኛል፡፡ የአላህን ውዴታ ያገኝ ሰው ደግሞ የዱዓውን ተቀባይነት ያገኛል፡፡
እነዚህን ትሩፋቶች ሶሰት ሐዲሦች ያረጋግጣሉ፡-
አቡ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸወን ይቀበላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ - የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- እንዲህ ብለዋል፤ ‹‹በርግጥ አላህ አንዲህ ብሏል፣- “ለእኔ ባላንጣ ያደረገን ሰው በርግጥ በጦርነት እጋፈጠዋልሁ፡፡ ባሪያዬ እኔ ግዴታ ካደረግኩበት ነገር ውጭ በእኔ ዘንድ ተወዳጅ በሆነ ነገር አይቃረብም፡፡ ባሪያዬ እከምወደው ድረስ ግዴታ ባልሆኑ ተግባራት ወደኔ ከመቃረብ አይታክትም፡፡ ከወደድኩት የሚሰማበትን መስሚያ ጆሮ፣ የሚያይበትን ዓይን፣ የሚዳስስበትን እጅ፣ የሚራመድበትን እግር እሆንለታለሁ፡፡ ከጠየቀኝ በርግጥ እሰጠዋለሁ፡፡ ጥበቃ ከጠየቀኝም በርግጥ እጠብቀዋለሁ፡፡ እኔ ክፉውን ነገር እንደምጠላለትና ሞትን ከሚጠላው የሙእሚን ነፍስ ይበልጥ ከምፈጽመው አንዳች ነገር ወደኋላ አልልምም፡፡”›› ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (6502) ላይ ሐዲሡን ዘግበውታል፡፡
4/ ግዴታ የሆኑ ተግባራት ሲጓደሉና ያልተሟሉ ሲሆኑ ግዴታ ያልሆኑ ተግባራት እነዚህን ያልተሟሉ ግዴታ የሆኑ ተግባራትን ይሞላሉ፡፡
ይህንንም የሚያረጋግጥልን ማረስጃ
አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- እንዲህ ማለታቸውን ሰምቻለሁ ብለዋል፣‹‹በትንሳኤ እለት አንድ የአላህ ባሪያ ከሥራዎቹ መካከል በቅድሚያ የሚተሳሰብበት ነገር ሰግዴቱ ነው፡፡ ስግደቱ ከተስተካከለች በርግጥ ነጻ ወጥቷል፡፡ ድልም ተቀዳጅቷል፡፡ ስግደቱ ከተበላሸችበት በርግጥ ከንቱ ሆነ ከሰረም፡፡ ግዴታ ከሆነበት ተግባሩ አንዳች ነገር ከጎደለ እጅግ የላቀውና ልእልና የተገባው አላህ ፤ “ባረያዬ በፈቀደኝነት የፈጸመው ተግባር አለን? እስኪ ተመልከቱ፡፡” ይላል፡፡ በፈቀደኝነት በሰራው ሥራ የጎደለው ይሟላለታል፡፡ ከዚያ ቀሪዎቹ ሥራዎቹ በዚያ ሁኔታ ላይ ይሆናሉ፡፡›› አቡ ዳዉድ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (864) እንዲሁም አት-ቲርሚዚይ በቁጥር (413) ሐዲሡን የዘገቡት ሲሆን አል-አልባኒ በትክክለኛ የሐዲሥ ዘገባ ድርሳናቸው ላይ ትክክለኛነቱን አጽድቀዋል፡፡ (ሰሒሑ-ል-ጃሚዕ ቅጽ ፡ 1 ገጽ፡ 405)