brightness_1
اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لَا إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ خَلَقْتَنِي، وَأَنَا عَبْدُكَ,وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ, أَبُوءُ لَكَ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوءُ لَكَ بِذَنْبِي فَاغْفِرْ لِي فَإِنَّهُ لَا يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ
ሰይዪዱ-ልኢስቲግፋር (ምህረት የመጠየቂያ ቃላት የበላይ)፡- “አልላሁምመ አንተ ረብቢ ላ ኢላሀ ኢልላ አንተ ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱክ፣ ወአነ ዐላ ዐህዲክ ወወዕዲክ ማስተጠዕቱ አዑዙ ቢከ ሚን ሸርሪ ማሰነዕቱ አቡዉኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለይየ ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ ፈግፊር ሊ ፈኢንነሁ ላ የግፊሩ-ዝዙኑዉበ ኢልላ አንተ፡፡ /አላህ ሆይ! አንተ ጌታዬ ነህ፡፡ ካንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ የፈጠርከኝ አንተ ነህ፡፡ እኔ ባሪያህ ነኝ፡፡ በምችለው አቅም በቃል-ኪዳንህና በቀጠሮህ ላይ ነኝ፡፡ በእኔ ላይ በለገስከው ጸጋዎችህ ወዳንተ እመለሳለሁ፡፡ በወንጀሎቼም ወዳንተ እመለሳለሁ፡፡ ወንጀሎቼን ማርልኝ፡፡ በርግጥ ካንተ በስተቀር ወንጀሎችን የሚምር ማንም የለም፡፡/” የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “እርግጠኛ ሆኖ በቀኑ ክፍለ-ጊዜ ላይ ያለና በዚያው ቀኑ ሳይመሽ የሞተ እንደሆነ እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው፡፡ እርግጠኛ ሆኖ ሌሊት ላይ ያለና በዚያው ሌሊት ላይ ሳያነጋ የሞተ እንደሆነ እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (6306) ላይ ዘግበውታል፡፡
.......