brightness_1
-በእጅጉ የላቀውና የተከበረው- አላህ እሱን በማውሳት ላይ በበርካታ ሥፍራዎች ላይ አደራ ብሏል፡፡
-በእጅጉ የላቀውና የተከበረው- አላህ እሱን በማውሳት ላይ በበርካታ ሥፍራዎች ላይ አደራ ብሏል፡፡ ከአብነት ያህልም፡-
1/ -በእጅጉ የላቀው- አላህ ባሪያዎ እሱን ማስታወስን እንዲያበዙ አደራ ብሏቸዋል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፣ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብዙ ማውሳትን አውሱት፡፡ በቀኑ መጀመሪያና መጨረሻም አጥሩት፡፡” (አል-አሕዛብ ፡ 41 – 42)፡፡
2/ -በእጅጉ የላቀው- አላህ እሱን የሚያወሱ ወንዶችንና ሴቶችን በምሕረት፣ በላቀ ምንዳና ሽልማት ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፣ “አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም አላህ ለነረትሱ ምሕረትንና ታላቅ ምንዳን አዘጋጅቶላቸዋል፡፡” (አል-አሕዛብ ፡ 35)፡፡
3/ አላህ -በእጅጉ የላቀውና የተከበረው- ከመናፍቃን መገለጫ ባሕሪያት አስጠንቅቆናል፡፡ መናፍቃን -በእጅጉ የላቀውና የተከበረው- አላህን ያስታውሳሉ፡፡ ነገር ግን እሰኪ ምን ያህል እንደሚያስተውሱት ከእኔ ጋር አስተውል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፣ “መናፍቃን አላህን ያታላሉ፤ እርሱም አታላያቸው ነው፤ (ይቀጣቸዋል)፤ ወደሰላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ሰዎችን የ፣የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፤ አላህንም ጥቂትን እንጂ አያወሱም፡፡” (አን-ኒሳእ ፡ 142)
4/ -እጅጉን የተከበረውና የላቀው- አላህ በሃብትና በልጆች እሱን ከማስታወስ እንዳንዘናጋ አስጠንቅቆናል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፣ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ አላህን ከማስታወስ አያጣሉዋችሁ፤ ይህንንም የሚሠሩ ሰዎች እነዚያ ከሳሪዎቹ ናቸው፡፡” (አል-ሙናፊቁን ፡ 9)
5/ እስኪ ይህን ታላቅ ትሩፋት፣ ታላቅ ክብር ከእኔ ጋር አስተውል፡፡ -በእጅጉ የላቀው አላህ- እንዲህ ብሏል፣ “አስታውሱኝ አስታውሳችኋለሁ” በሐዲሥ አል-ቁድሲይ ላይ ደግሞ እንዲህ ብሏል፣ “እኔ ባሪያዬ በእኔ ላይ እንደጠረጠረኝ ነኝ፡፡ካወሳኝ እኔ ከእሱ ጋር ነኝ፡፡ በራሱ ካስታወሰኝ በራሴ አስታውሰዋለሁ፡፡ ከሰዎች ጋር ካስታወሰኝ ከእነሱ ከተሻሉት ጋር ሆኜ አስታውሰዋለሁ፡፡” ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (7405)፣ ሙስሊም በቁጥር (2675) ከአቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ዘግበውታል፡፡