የላቀው፡- የአላህ ንግግር የሆነውን ቁርኣንን ማንበብ ነው፡፡ እሱን በመቅራት አምልኮታዊ ተግባር የቀደምት መልካም ትውልዶች ዓይኖች በርካታ ሌሊቶችን ካለ እንቅልፍ አሳልፈዋል፡፡ መኝታዎቻቸውንም ረስተዋል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፣ “ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበር፡፡ በሌሊት መጨረሻዎችም እነሱ ምሕረትን ይጠይቃሉ፡፡” (አዝ-ዛሪያት ፡ 17 – 18)፡፡ እነዚህ ትውልዶች ሌሊታቸውን ቁርኣን በመቅራትና ሌሎች በአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ሐዲሥ የተዘገቡ አዝካሮችን በማለት ከንጋቱ ጋር ያገናኙ ነበር፡፡ አላህ ምስጋና ይገባው በባለቤቶቹ ምን ያህል ያማረ ሌሊት ነው! እኛስ አላህ ይሁነን፡፡ ስንትና ስንት ሌሊቶችን ዘንግተን ከስረናል፡፡ ሌሊቶቻችንን ምሽቶቻችንን በከንቱ በማሳለፋችንና በእነሱ ላይም በማጓደላችን ከስረናል፡፡ ምናልባት ከእኛ መካከል ጌታችን ያዘነለት ካልሆነ በስተቀር አምላካችንን መወንጀላችንን ለእሱ አሳልፈን ሰጥተናል፡፡
ሐምማድ ኢብን የዚድ እንዳስተላለፉተና ዐጣእ ኢብን አስ-ሳኢብ እንዳወሩት አባ ዐብዱርረሕማን እንዲህ ብለዋል፣ “ቁርኣንን አስር አንቀጽ ከተማሩ በኋላ በእነሱ ሳይተገብሩ ወደሌሎች አስር አንቀጾች ከማይሻገሩት ሕዝቦች ተምረናል፡፡ቁርኣንን ከተግባር ጋር እንማር ነበር፡፡ ከእኛ በኋላ ቁርኣንን እንደውሃ መጠጣት የሚጠጡና ሥሮቻቸውን ላይ የማይደርስ የሆኑ ሕዝቦች ይወርሱታል፡፡” ሰየር አዕላሙ-ንኑበላእ ቅጽ፡ 4 ገጽ ፡ 269፡፡
በተለይ በአሁኑ ሩጫዎች በበዙበት ዘመን አብዛኛዎቻችን የልቦናችንን መዛግና አላህን ከማስታወስ መዘናጋት አስመልክተን ስሞታ እናቀርባለን፡፡ ልቦና ሕይወት የሚኖረው አላህን በማውሳት (በዚክር ) ነው፡፡ ከአቡ ሙሳ አል-አሽዐሪይ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንደተላለፈው ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ጌታውን የሚያወሳና የማያወሳ ምሳሌ እንደሕያውና ሙት ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ቡኻሪ ዘግበውታል፡፡ በሙስሊም የሐዲሥ ዘገባ ደግሞ ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “በውስጡ አላህ የሚወሳበት ቤትና የማይወሳበት ቤት ምሳሌ እንደሕያውና ሙት ነው፡፡” ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (6407)፣ ሙስሊም በቁጥር (779) ላይ ዘግበውታል፡፡
-በእጅጉ የላቀውና የተከበረው- አላህ እሱን በማውሳት ላይ በበርካታ ሥፍራዎች ላይ አደራ ብሏል፡፡ ከአብነት ያህልም፡-
1/ -በእጅጉ የላቀው- አላህ ባሪያዎ እሱን ማስታወስን እንዲያበዙ አደራ ብሏቸዋል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፣ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብዙ ማውሳትን አውሱት፡፡ በቀኑ መጀመሪያና መጨረሻም አጥሩት፡፡” (አል-አሕዛብ ፡ 41 – 42)፡፡
2/ -በእጅጉ የላቀው- አላህ እሱን የሚያወሱ ወንዶችንና ሴቶችን በምሕረት፣ በላቀ ምንዳና ሽልማት ቃል ገብቶላቸዋል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፣ “አላህን በብዙ አውሺዎች ወንዶችና አውሺዎች ሴቶችም አላህ ለነረትሱ ምሕረትንና ታላቅ ምንዳን አዘጋጅቶላቸዋል፡፡” (አል-አሕዛብ ፡ 35)፡፡
3/ አላህ -በእጅጉ የላቀውና የተከበረው- ከመናፍቃን መገለጫ ባሕሪያት አስጠንቅቆናል፡፡ መናፍቃን -በእጅጉ የላቀውና የተከበረው- አላህን ያስታውሳሉ፡፡ ነገር ግን እሰኪ ምን ያህል እንደሚያስተውሱት ከእኔ ጋር አስተውል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፣ “መናፍቃን አላህን ያታላሉ፤ እርሱም አታላያቸው ነው፤ (ይቀጣቸዋል)፤ ወደሰላትም በቆሙ ጊዜ ታካቾች ሰዎችን የ፣የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፤ አላህንም ጥቂትን እንጂ አያወሱም፡፡” (አን-ኒሳእ ፡ 142)
4/ -እጅጉን የተከበረውና የላቀው- አላህ በሃብትና በልጆች እሱን ከማስታወስ እንዳንዘናጋ አስጠንቅቆናል፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፣ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ አላህን ከማስታወስ አያጣሉዋችሁ፤ ይህንንም የሚሠሩ ሰዎች እነዚያ ከሳሪዎቹ ናቸው፡፡” (አል-ሙናፊቁን ፡ 9)
5/ እስኪ ይህን ታላቅ ትሩፋት፣ ታላቅ ክብር ከእኔ ጋር አስተውል፡፡ -በእጅጉ የላቀው አላህ- እንዲህ ብሏል፣ “አስታውሱኝ አስታውሳችኋለሁ” በሐዲሥ አል-ቁድሲይ ላይ ደግሞ እንዲህ ብሏል፣ “እኔ ባሪያዬ በእኔ ላይ እንደጠረጠረኝ ነኝ፡፡ካወሳኝ እኔ ከእሱ ጋር ነኝ፡፡ በራሱ ካስታወሰኝ በራሴ አስታውሰዋለሁ፡፡ ከሰዎች ጋር ካስታወሰኝ ከእነሱ ከተሻሉት ጋር ሆኜ አስታውሰዋለሁ፡፡” ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (7405)፣ ሙስሊም በቁጥር (2675) ከአቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ዘግበውታል፡፡
1. አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “አንድ መቶ ጊዜ ላ ኢላሀ ኢልለልላህ ወሕደሁ ላ ሸሪይከ ለህ ለሁልሙልኩ ወለሁልሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲይር አስር ጫንቃዎችን ነጻ ከማውጣት ጋር ምንዳው ሲስተካከልለት አንድ መቶ ምንዳዎች ይጻፉለታል፣ አንድ መቶ ሐጢአቶችም ይሰረዩለታል፣ ይህች ቃልም በዚያ ቀን እስኪያመስ ድረስ ከሸይጣን ጥበቃ ትሆንለታለች፡፡ እሱ ከሰራው ሥራ የተሻለ ሥራ ሰርቶ ማንም አይመጣም እሱ የሰራውን ዓይነት ሥራ አብዝቶ ሰርቶ ከሚመጣ ሰው በስተቀር፡፡ በቀን ውስጥ አንድ መቶ ጊዜ ሱብሓነ-ልላህ ወልሐምዱሊልላህ ያለ ሐጢአቶቹ የባሕር አረፋ ያህል ቢሆኑም ይሰረዩለታል፡፡” ብለዋል፡፡ ቡኻሪ ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (3293)፣ ሙስሊም ደግሞ በቁጥር (2691) ላይ ዘግበውታል፡፡
አቢ አዩብ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “አስር ጊዜ በመደጋገም ላ ኢላሀ ኢልለልላህ ወሕደሉ ላ ሸሪክ ለሁ ለሁልሙልኩ ወለሁልሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲይር ያለ ከኢማዒል ልጆች አራት ነፍሶችን ነጻ እንዳደረገ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (6404)፣ ሙስሊም ደግሞ በቁጥር (2693) ላይ ሐዲሡን ዘግበውታል፡፡
3. ሰዕድ ኢብን አቢ ወቅቃስ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት፣ ‹‹ከአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ዘንድ ነበርን፡፡ እንዲህም አሉን፣ “አንዳችሁ በየእለቱ አንድ ሺህ ምንዳዎችን ማግኘት ይሳነዋልን?” አሉ፡፡ አብረውን ከተቀመጡት ሰዎች መካከል አንዱ ጠያቂ፣ ‹አንዳችን እንዴት ሆኖ ነው አንድ ሺህ ምንዳዎችን ሊያገኝ የሚችለው?› በማለት ጠየቃቸው፡፡ እሳቸውም፣ “አንድ መቶ ተስቢሖችን ያደርጋል፡፡ አንድ ሺህ ምንዳዎችም ይጻፉለታል ወይም አንድ ሺህ ሐጢአቶች ይሰረዩለታል፡፡” አሉ፡፡›› ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2698) ላይ ዘግበውታል፡፡
4. አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ሱብሓነ-ልላህ ወቢሐምዲሂ ያለ ሐጢአቱ የባሕር አረፋ ያህል ቢሆኑም ይሰረዩለታል፡፡” ብለዋል፡፡ ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (6405)፣ ሙስሊም በቁጥር (2692) ሐዲሡን የዘገቡት ሲሆን በሌላ የሙስሊም ዘገባ፣ “ሲያነጋና ሲያመሽ መቶ ጊዜ፣ ሱብሓ-ልላሂ ወቢሐምዲሂ ያለ በትንሳኤ እለት ከእሱ የተሻለ ሥራ ሰርቶ የሚመጣ ሰው አይኖርም እርሱ ያለውን ካለ ወይም በእሱ ላይም ጨምሮ የመጣ ሰው ካልሆነ በስተቀር፡፡” ብለዋል፡፡ ሙስሊም ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2692) ላይ ዘግበውታል፡፡
የዚክርን ዓይነቶችና ትሩፋቶች የሚወሱ ሐዲሦች በርግጥ በቁጥር እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ ከዚህ በላይ የተጠቀሰው ዚክርን አስመልክቶ ከተዘገቡት ሐዲሦች ሁሉ ይበልጥ ትክክለኛውና ተቀባይነት ያለው ነው፡፡ ዚክርን አስመልክቶ ከዚህ ሐዲሥ ሌላ በርካታ ሐዲሦች ተዘግበዋል፡፡ አቢ ሙሳ አል-አሽዐሪይ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት፣ ‹‹የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ከጀነት ሃብቶች መካከል ከሆኑት ላመላክትህን?” አሉኝ፡፡ እኔም፡- እንዴታ! አልኳቸው፡፡ እሳቸውም፣ “ላ ሐውለ ወላ ቁውወተ አልላ ቢላልህ፡፡ /ብልሐትም፣ ብርታትም በአላህ ካልሆነ በስተቀር በሌላ የለም፡፡/” በል አሉኝ፡፡›› ብለዋል፡፡ ቡኻሪ ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (4202)፣ ሙስሊም በቁጥር (2704) ላይ ዘግበውታል፡፡
አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ስብሓነ-ልላሂ ወልሐምዱሊልላሂ ወላ ኢላሀ ኢልለልላሁ ወልላሁ አክበር ማለቴ በኔ ዘንድ ጸሐይ ከወጣችበት ቀን ይበለት እጅጉን ተወዳጅ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ሙስሊም ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2695) ላይ ዘግበውታል፡፡
ኢስቲግፋር (ከአላህ ምሕረት መጠየቅ) እንዲሁ የዚክር ዓይነቶች ነው፡፡ ከዚህ በላይ በሙስሊም ከአል-አገርር -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- የተዘገበው ሐዲሥ ተጠቅሷል፡፡ እንዲሁም፣ “ብልቀልቢ፣ በርግጥ በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ አላህን ምሕረት እጠይቃለሁ፡፡” ብለዋል፡፡ ሙስሊም ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2702) ላይ ዘግበውታል፡፡
ይህ የነቢዩ -የአላህ እዝንትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ተግባር ነው፡፡ በአንደበታቸውም በኢስቲግፋር (ምህረትን ከአላህ በመጠየቅ) ላይ አነሳስተዋል፡፡ በሙስሊም ትክክለኛ የሐዲሥ ዘገባ ከአል-አገርር -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንደተላለፈው የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ሰዎች ሆይ! ወደአላህ በንሰሃ ተመለሱ፡፡ በቀን ውስጥ በርግጥ እኔ መቶ ጊዜ ወደርሱ በንሰሃ እመለሳለሁ፡፡” ብለዋል፡፡ ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2702) ላይ ዘግበውታል፡፡
ቡኻሪ ከአቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው በዘገቡት ሐዲሥ አቢ ሁረይራህ፣ ‹‹የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝንትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “በአላህ እምላለሁ! በቀን ውስጥ በርግጥ ከሰባ ጊዜ በላይ አላህን ምሕረት እጠይቃለሁለ፣ ወደርሱም በንሰሃ እመለሳለሁ፡፡” ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡›› ብለዋል፡፡ ቡኻሪ ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (6307) የዘገቡት ሲሆን ማንኛውም የአላህ ባሪያ ከአላህ ምሕረትን ከመጠየቅ መዘናጋት አይገባውም፡፡
የዚክር ነቢያዊ ፈለግን -እንዲሁም ሁሉንም እለታዊ የሆኑ ነቢያዊ ፈለጎችን- በቡኻሪና በሙስሊም ዘግበውታል፡፡ ዚክሩም አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ያስተላለፉት ሲሆን የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “በምላስ ላይ ቀላል፣ በሚዛን ላይ ከባድ፣ እጅግ በጣም አዛኝ በኾነው ጌታ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ቃላት፡- ሰብሓነ-ልላሂ ወቢሐምዲሂ፣ ሱብሓነ-ልላሂ-ልዐዚይም ናቸው፡፡” ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሓዲሥ ዘገባ ቁጥር (6406)፣ ሙስሊም በቁጥር (2694) ፣ላይ ዘግበውታል፡፡
በጸጋዎቹ መልካም የሆኑ ነገሮች የሚሟሉ ለሆኑት አላህ ምስጋና ይሁን