ከማፋሸግ ነቢያዊ ፈለጎች መካከል ማፋሸጉን መደበቅ ወይም በእጅ መመለስ ነው፡፡
ለዚህ ማስረጃው፡-
አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “”የሚያነጥሱ ሰዎችን አላህ ይወዳል፡፡ ማፋሸግንም ይጠላል፡፡ አንድ ሰው አነጥሶት አላህን ካመሰገነ ሲያስነጥስ በሰሙት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ አላህ ይማርህ የማለት ግደታ አለባቸው፡፡ ማፋሸግ ግን በርግጥ እሱ ከሸይጣን ነው፡፡ በተቻለው አቅም ይመልሰው፡፡ ሰውየው፣ ‹ሃ...ህ› ካለ ሸይጣን በእሱ ይስቃል፡፡” ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2663) ላይ ዘግበውታል፡፡
ሙስሊም ከአቢ ሰዒድ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-በዘገቡት ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “አንዳችሁ ካፋገ አፉን በእጁ ይያዝ፡፡ በርግጥ ሸይጣን ይገባልና ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2995) ላይ ዘግበውታል፡፡ ማፋሸግን መደበቅ አፍን በመዝጋት ይህም አፍ እንዳይከፈት በማድረግ ወይም ከንፈርን በጥርሶች አጥብቆ በመያዝ ወይም እጅን አፍ ላይ በማድረግ ወ.ዘ.ተ በመሳሰሉት ሊፈጸም ይችላል፡፡
ለሚያፋሽግ ሰው ሲያፋሽግ ድምጹን ማድረግ የለበትም፡፡
ለሚያፋሽግ ሰው ሲያፋሽግ ድምጹን ማድረግ የለበትም፡፡ ለምሳሌ፣‹‹ህ…ሃ....ኣህ›› ወይም ‹‹ኣኣኣኣ…..ህ›› ወ.ዘ.ተ እንደመሳሰሉት ዓይነቶችን ድምጽ በማውጣት ማፋሸግ የለበትም፡፡ ይህ ሸይጣን በእሱ ላይ እንዲስቅበት የሚያደርገው ጥሪ ነው፡፡
ለዚህ ማስረጃው፡-
አቢ ሁረያራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ማፋሸግ ከሸይጣን ነው፡፡ አንዳችሁ ካፈሸገ በተቻለው አቅም ይመልሰው፡፡ ‹ሃ….ህ› ካለ ሸይጣን ይስቃል፡፡” ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (3298)፣ ሙስሊም ደግሞ በቁጥር (2994) ላይ ዘግበውታል፡፡
ማሳሳቢያ፡-
አንዳንድ ሰዎች ከፋሸጉ በኋላ ከሸይጣን በአላህ መጠበቅ ልማዳቸው አድርገውታል፡፡ ነገር ግን ይህ ምንም ዓይነት ማስረጃ የሌለውና የነቢዩን -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ፈለግን መቃረንን የሚያስከትል ተግባር ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ዓይነቶቹ ሰዎች እዚህ ቦታ ላይ ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ያላሉትን ዚክር በራሳቸው ፈጥረው አምጥተዋልና ነው፡፡