ከዐስር በፊት የተገደበ የሱንና ሰላትን መስገድ ነቢያዊ ፈለግ አይደለም፡፡
ሸይኹ-ል-ኢስላም ኢብን ተይሚያህ -አላህ ይዘንላቸው-፣ ‹‹ከዐስር በፊትን በተመለከተ ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- ከዐስር በፊት ይሰግዱ ነበር ብሎ የተናገረ አንድም የለም፡፡ አለ ከተባለም በሐዲሡ ላይ ድክምት እንዲውም ስህተት የሆነ ካልሆነ በስተቀር ምንም የለም፡፡›› ብለዋል፡፡ አል-ፈታዋ ቅጽ ፡ 23 ገጽ፡ 125፡፡
ትክክለኛው -አላህ ይበልጥ ዐዋቂ ነው-፡- ከዐስር በፊት የተገደበ የሱንና ሰላትን መስገድ ነቢያዊ ፈለግ አይደለም፡፡ ስለዚህ ይህ ጉዳይ ያልተገደበ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት ሰላት መስገድ ክልክል ከሆነበት ወቅት ውጭ ልክ በማንኛውም ወቅት እንደሚሰገደው የፈለገ ሰው ሁለት ረከዐህ ወይም ከዚያ በላይ በራሱ ፍላጎት ሊሰግድ ይችላል፡፡ ነገር ግን የተገደበ የሆነ ሰላት ከዐስር ሰላት በፊት የለም፡፡