languageIcon
አማርኛ
አማርኛ
العربية
Azeri
বাংলা
Bosanski
Deutsch
English
Español
Filipino
فارسي
Français
(Hausa) هَوُسَ
हिन्दी
Indonesia
italiano
Қазақ тілі
தமிழ்
كوردی
नेपाली
Português
Pусский
සිංහල‎
Gjuha shqipe
Kiswahili
ภาษาไทย
Türkçe
Українська
اردو
Yorùbá
中文
search
search
በአድ-ዱሓ ወቅት አንድ የአላህ ባሪያ የአድ-ዱሓ ሰላት መስገዱ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡

ለዚህ ማስረጃው፡-

ሀ. አቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው-፣ ‹‹ወደጄ የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- በሶሰት ነገሮች ላይ አደራ ብለውኛል፡፡ -እነርሱም፡- ከእያንዳንዱ ወር ሶሰት ቀናትን በመጾም፣ በአድ-ዱሓ ሁለት ረከዐዎችና ከመተኛቴ በፊት ዊትር በመስገድ ላይ ናቸው፡፡›› ብለዋል፡፡ እንደዚሁም ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- አባ ደርዳእን -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- በዚሁወ ላይ አደራ ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ሙሰሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (722) ላይ ዘግበውታል፡፡ አባ ዘርንም -አላህ  መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- አድራ ብለዋል፡፡ ሐዲሡን አን-ነሳኢይ በአስ-ሱነኑ-ልኩብራ መጽሐፋቸው በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (2712) ላይ ዘግበውታል፡፡ አል-አልበኒይም የሐዲሡን ትክክለኛነት አረጋግጠዋል፡፡ አስ-ሰሒሐህ 2166፡፡

ለ. አቢ ዘር -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ከእናንተ መካከል የአንዳችሁ የአካል መገጣጠሚያዎች ሁሉ ሰደቃህ ጸንቶባቸው ያነጋሉ፡፡ እያንዳንዱ ተስቢሕ (ሱብሐነልላህ) ሰደቃህ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተሕሚድ (አልሐምዱሊላህ) ሰደቃህ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተህሊል (ላኢላሀ ኢልለሏህ) ሰደቃህ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተክቢር (አላሁ አክበር) ሰደቃህ ነው፡፡ በመልካም ማዘዝ ሰደቃህ ነው፡፡ ከመጥፎ መከልከልም ሰደቃህ ነው፡፡ በአድ ዱሓ የሚሰግዳቸው ሁለት ረከዐዎች እነዚህን ሁሉ (በምንዳ) ያብቃቁታል (ይስተካከሉታል)፡፡” ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (720) ላይ ዘግበውታል፡፡

ሙሰሊም በትክክለኛ የሐዲሥ ዘገባቸው ከዓኢሻህ -አላህ መላክም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- አንድ ሰው ከሶሰት መቶ ስልሳ መገጣጠሚያዎች በርግጥ የተፈጠረ መሆኑንና በትንሳኤ እለት በእነዚህ መገጣጠሚያዎች ሰደቃ ይዞ የመጣ በዚያን ወቅት ራሱን ከጀሃነም እሳት ነጻ አውጥቶ እንሚሄድ ያብራሩበትን ሐዲሥ ዘግበዋል፡፡

 
Simple Audio Player
 
facebook googleplus twitter