brightness_1
የሰላት መክፈቻ ዱዓእ ማድረግ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡
የሰላት መክፈቻ ዱዓእ አገላለጽ የተለያየ ነው፡፡ ይህን ዱዓእ በተለያየ ሁኔታ ማለት የተወደደ ነው፡፡ በሐዲሥ ላይ ከተዘገቡ የሰላት መክፈቻ ዱዓእ መካከል፡-
ሀ. ‹‹ሱብሓነከ-ልላለሁምመ ወቢሐምዲከ፣ ወተባረከ-ስሙከ፣ ወተዓላ ጀድዱከ ወላ ኢላሀ ገይሩከ፡፡/ጠራት የተገባህ አላህ ሆይ! ምስጋናም ላንተ ነው፡፡ ስምህም የተባረከ ነው፡፡ ክብርህም የላቀ ነው፡፡ በእርግጥ ካንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡/›› አህመድ ሐዲሡን በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (11473)፣ አቡ ዳዉድ በቁትር (776)፣ አት-ቲርሚዚይ በቁጥር (243) እንዲሁም አን-ነሳኢይ በቁጥር (900) ዘግበውታል፡፡ ሐዲሡ የሚጠናከርበት የተለያዩ መንገድች ያሉ ሲሆን ኢብን ሐጀር የሐዲሡን በጥሩ ደረጃ መገኘት አረጋግጠዋል፡፡ (አል-አፍካር ቅጽ ፡ 1 ገጽ ፡ 412)፡፡
ለ. ‹‹አል-ሐምዱ-ሊልላሂ ሐምደን ከሢይረን ጠይዪበን ሙባረከን ፊይሂ /በርካታ፣ ያማረና በርከት ያለበት ምስጋና ለአላህ ነው፡፡/›› የዚህ ምስጋና ትሩፋት አስመልከተው የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን- እንዲህ ብለዋል፣ “ማናቸው ያነሷት ዘንድ አስራ ሁለት መላእክቶች ሲሽቀዳደሙባት በርግጥ ተመልክቻለሁ” ሐዲሡን ሙሰሊም ከአንስ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (600) ዘግበውታል፡፡
ሐ. “አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጣያየ ከማ በዐድተ በይነ-ል-መሽሪቂ ወል-መግሪብ፡፡ አልላሁምመ ነቅቂኒ ሚን ኸጣያየ ከማ ዩነቀ አሥ-ሠውቡ-ል-አብየዱ ሚነ-ድደነስ፡፡ አልላሁምመ ኢግሲልኒ ሚን ኸጣያየ ቢሥሠልጂ ወል-ማኢል ወል-በረዲ፡፡/አላህ ሆይ! በምስራቅና በምዕራብ እንዳራራቅከው በእኔና በሐጢአቶቼ መካከል አራርቅ፡፡ አላህ ሆይ! ነጭ ልብስ ከእድፍ እንደሚነጻ ሁሉ ከሐጢአቶቼ አንጻኝ፡፡ አላህ ሆይ! በበረዶ፣በውሃና በበቀቅ ከሐጢአቶቼ እጠበኝ፡፡/” ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (744)፣ ሙስሊም ደግሞ በቁጥር (598) ከአቢ ሁረይራህ -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ዘግበውታል፡፡
መ. “አለሁ አክበር ከቢራ፣ ወልሐምዱ ሊልላሂ ከሲይራ፣ ወሱበሓነ-ልላሂ ቡክረተን ወአሲይላ፡፡/አላህ በእጅጉ መተለቅን ታላቅ ነው፡፡ በርካታ ምስጋና ለአላህ ይገባው፡፡ አላህ ዛሬም ምንጊዜም ከሚባለው ውድቅና የማይረባ ንግግር የጠራ ነው፡፡” የዚህን ዱዓእ ትሩፋት አስመልክተው የአላህ መልእክተኛ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “በጣም ተደነቄላታለሁ፡፡ የሰማያት በሮች ተከፈቱላት፡፡” ብለዋል፡፡ ሐዲሡን ሙስሊም በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (601) ከዚህ በላይ ባሳለፍነው የኢብን ዑመር -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- ዘግበውታል፡፡