brightness_1
ሌሊት ላይ ከእንቅልፉ የነቃ ሰው ይህን ዚክር ማለቱ ነቢያዊ ፈለግ ነው፡-
ከዑባደህ ኢብን አስ-ሳሚት -አላህ መልካም ሥራዎቻቸውን ይውደድላቸው- እንዳስተላለፉት ነቢዩ -የአላህ እዝነትና ሰላምታ በእሳቸው ላይ ይሁን-፣ “ሌሊት ላይ ድንገት የነቃና ላ ኢለሀ አልለልላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ-ልላህ ለሁ-ልሙልኩ ወለሁ-ልሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲይር አልሐምዱሊልላህ የሱብሓነ-ልላህ ወላ ኢላሀ ኢልለልላህ ውልላሁ አክበር ወላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢልላ ቢልላህ፡፡ /ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ብቻውን ነው፡፡ አጋር የለውም፡፡ ንግሥና ለሱ ነው፡፡ ምስጋናም ለእሱ ነው፡፡ እርሱ በሁለም ነገር ላይ ቻይ ነው፡፡ ምስጋና ለአላህ ይሁን፡፡ ከከንቱና ውድቅ ንግግሮች አላህ በእጅጉ ጠራ፡፡ ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለምም፡፡ አላህ ታላቅ ነውም፡፡ ብልሐትም ሆነ ሃይል በአላህ ካልሆነ በስተቀር በሌላ የለም፡፡/ ያለና ከዚያም አልላሁምመ ኢግፊር ሊ፡፡ /አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማርልኝ፡፡/ ወይም ዱዓእ ካደረገ ዱዓው ምላሽ ያገኛል፡፡ ዉዱእ አድርጎ ከሰገደ ሰላቱ ተቀባይነትን ያገኛል፡፡” ሐዲሡን ቡኻሪ በሐዲሥ ዘገባ ቁጥር (1154) ላይ ዘግበውታል፡፡
ኢብን አሢር -አላህ ይዘንላቸው-፣ ‹‹“ሌሊት ላይ ድንገት የነቃ” ማለት ከእንቅልፉ የባነነ ማለት ነው፡፡›› ብለዋል፡፡ ኢብን አሢር፡- አን-ኒሃያ ፊ ገሪቢ-ልአሠር ገጽ ፡ 108፡፡
በዚህ ሐዲሥ ውስጥ ሁለት የላቁ የሆኑ ብስራቶች አሉ፡፡ እነርሱም፡- ከእንቅልፉ ድንገት ነቅቶ፣ “ላ ኢለሀ አልለልላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ-ልላህ ለሁ-ልሙልኩ ወለሁ-ልሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲይር አልሐምዱሊልላህ የሱብሓነ-ልላህ ወላ ኢላሀ ኢልለልላህ ውልላሁ አክበር ወላ ሐውለ ወላ ቁውወተ ኢልላ ቢልላህ፡፡ /ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ብቻውን ነው፡፡ አጋር የለውም፡፡ ንግሥና ለሱ ነው፡፡ ምስጋናም ለእሱ ነው፡፡ እርሱ በሁለም ነገር ላይ ቻይ ነው፡፡ ምስጋና ለአላህ ይሁን፡፡ ከከንቱና ውድቅ ንግግሮች አላህ በእጅጉ ጠራ፡፡ ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለምም፡፡ አላህ ታላቅ ነውም፡፡ ብልሐትም ሆነ ሃይል በአላህ ካልሆነ በስተቀር በሌላ የለም፡፡/” የሚለውን ዚክር ያለ ሰው ሁለት ብስራቶች አሉት፡፡
አንደኛው፡- “አልላሁምመ ኢግፊር ሊ /አላህ ሆይ! ወንጀሌን ማርልኝ፡፡/ ወይም ዱዓእ ካደረገ ዱዓው ምላሽ ያገኛል፡፡”
ሁለተኛ፡- ተነስቶ ዉዱእ አድርጎ ከሰገደ ሰላቱ ተቀባይነት አለው፡፡ እነዚህን ችሮታዎች ላጣቀመን አላህ ምስጋና ይገባው፡፡ ለተግባሩ አጋጣሚውን እንጠይቀዋለን፡፡